Pages

Tuesday, April 8, 2014

ኒቆዲሞስ ዘሐሙስ (ሆሳዕና)



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 1 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 ዙፋኑን በሚንቦገቦግ የእሳት ሰረገላ ላይ ያደረገ፣ በእሳት መጋረጃዎች የሚሰወር፣ በምሥጋናም መብረቅ የሚጋረድ፣ በኪሩቤል የሚመሰገን፣ በሱራፌልም የሚወደስ እስራኤል ያመሰገኑት አንድ አምላክ በሥልጣንና በቻይነት የሰለጠነ በሆነ በእግዚአብሔር ስም ሰላም ይሁንላችሁ:: (መጽሐፈ ምሥጢር)


 ሶበ ንነውም ተወኪለነ መስቀለ ወሶበ ንትነሣእበተኛን ጊዜ መስቀልን ታምነን ነው፤ ከእንቅልፋችን በነቃን ጊዜም መስቀሉን እናስባለን፤ በስራችን በተሰማራን ጊዜ መስቀሉን እናስባለን፤ ተሰማርተን በምሥጋናና በጸሎት በምንገባ ጊዜ መስቀሉን ተደግፈን አስበን ነው::” ትላንትን በምሥጋና እንዳሳለፍን የድኅነታችን ፍጻሜ በተሰጠበት መስቀል ላይ ሃሳባችንን ጥለን ዛሬም ለቀን ውሎአችን እንነሳለን:: ስራችን ሁሉ ከሥጋ በተለየ አንተን ማመስገን ነው:: ሆሳዕና ለእግዚአብሔር ልጅ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በተዋሕዶ ለከበረው ሆሳዕና ለቤተክርስቲያን ራስ ሆሳዕና::

 ወትቤ ኢየሩሳሌም እምአይቴ ይመጽእ ንጉሥየኢየሩሳሌም ንጉሤና አምላኬ ከየት ይመጣል ትላለች:: ከቅድስት ሃገር ከኢየሩሳሌም ከኤሌዎን ተራራ::” ኢየሩሳሌም የሃዲሲቷ የሰላም ሃገር ልጆች ክርስቲያኖች ንጉሣቸውን ከቤቱ ከቤተክርስቲያን ይፈልጉታል:: እርሱምንጉሥኪ ጽዮን ጻድቀ ይመጽእጽዮን ሆይ ጻድቅ ንጉሥሽ ይመጣል፤ በአህያ ላይ ይጫናል፤ ልብሱን በወይን ያጥባል (ዘፍ 4910):: በአርያም ሆሳዕና በአርያም ሲሉ ቃል ተሰማ፤ አይሁድም ሊቅ (መምህር) ሆይ ደቀመዛሙርትህን ገስጻቸው አሉት ዝም ይሉ ዘንድ:: ኢየሱስም እንዲህ አላቸው እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮሃሉ::” ይላቸዋል፤ ልብና ደም አየርም ከማይመላለስበት የሕያውነት ምልክት ከሌለበት ድንጋይ እንኳን ምሥጋናን የሚያዘጋጅ አምላክ ነው:: ዛሬ ከድንጋይ አንሰን ይሆን ለጸሎት ለምሥጋና ጊዜ የሌለን አፋችን የተዘጋው? እርሱ ግን በአህያ ተቀምጦ ሕያዋን ከግዑዛን ጋር እያመሰገኑት በኋላው በፊቱ ከበውት ኢየሩሳሌም ገባ:: ኢሳይያስ አሰምቶ እንደተናገረ ኢየሩሳሌም ሆይ ብርሃንሽ ይብራ፤ ደስ ይበልሽ፤ ንጉሥሽ መጥቷልና::

 ይትናገሩ ሰላመ በእንቲአኪየእግዚአብሔር ሃገሩ ስለአንቺ ሰላምን ይናገራሉ፤ እንዲህ ሲሉ፡- ሕፃናትና አዋቂዎች ሆሳዕና በአርያም እያሉ ያመሰግናሉ፡፡ የእግዚአብሔር ምሥጋና ብርሃኑም በአንቺ ላይ ወጣ::” የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ አላቸው፤ ቀንደመለከትን ነፉ፤ ዘንባባን አነጠፉ፤ በአንድነትም አመሰገኑ::

ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ዲበ ዕዋለ አድግ ነበረበኪሩቤል ላይ የሚኖር በአህያ ላይ ተቀመጠ፤ በበረት ውስጥ ተጠቀለለ፤ በእንጨት መስቀል ተሰቀለ፤ በመስቀሉ እኛ ዳንን::” ሁሉ በእጁ የሆነ በአህያ ጀርባ ተቀመጠ፤ በድሃ ማደሪያ ተወለደ፤ በርግማን እንጨት ተሰቀለ:: እዩ በዚህ ዓለም በተናቀው ሁሉ የእኛን ጥበብ ከንቱ አደረገው::

 ይጠፍር በማይ ጽርሖ ወየሐጽብ በወይን ልብሶጠፈርን በውሃ ይታታል፤ የወይን ፍሬ ደም ለብሶ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ የአህያውን ውርንጭላ በወይን ሐረግ ላይ ያስራል፤ እነሆ ዋጋው ከእርሱ ጋር ያለው ይመጣል::” ጥርሶቹ እንደ በረዶ ነጭ እንደ ወተት የነጹ እንደ ወይን አይኖቹ ደስ ያላቸው ናቸው:: ጽዮን ሆይ ንጉሥሽ ጻድቅና የዋሕ ሆኖ ይመጣል:: ያዕቆብ ይሁዳ ልጁን ባረከው እንዲህ አለው ከአንተ ዘንድ ንጉሥ ይወጣል::

 ሁሩ በልዋ ወንግርዋ ለወለተ ጽዮንሂዱ ለጽዮን ልጅ ንገሯት እንዲህም በሏት፡- ኢየሱስ ንጉሥሽ በአህያ ተጭኖ እነሆ፤ በፊቱ ሰላምና ፍቅር አለ::” ሰላሙን ይስጠን::

No comments:

Post a Comment