Pages

Monday, March 30, 2015

ትምህርተ ሃይማኖት - ክፍል ስምንት

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ መጋቢት 22 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
        ውድ የመቅረዝ ተከታታዮች! እንዴት አላችኁ? ባለፉት ሰባት ተከታታይ ትምህርቶች ስለ መሠረታዊው ትምህርተ ክርስትና ደኅና አድርገን ለመማማር ሞክረናል፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱ ኾኖ ዛሬም በዚኽ ክፍል ተገናኝተናል፡፡ እግዚአብሔርም ያስተምረናል፡፡

Thursday, March 26, 2015

ኃጢአቴን በዝርዝር አለመናዘዜ አስጨነቀኝ፡፡ ምን ላድርግ?



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ መጋቢት 17 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ውድ መቅረዛውያን እንዴት አላችኁ? በዛሬው ጽሑፌ ከአንባብያን ከተላኩልኝ ጥያቄዎች ለኹለተኛው ጥያቄ የተሰጠውን ምላሽ አቀርብላችኋለኁ፡፡ መልሱን የሚሰጡን በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል እንዲኹም በታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳም የመጻሕፍተ ሐዲሳት የ5ኛ ዓመት ደቀ መዝሙር የኾኑት ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ናቸው፡፡ የልድያን ልቡና የከፈተ አምላክ የእኛንም እዝነ ልቡናችን ይክፈትልን፡፡ አሜን!

ጥያቄ፡- ሰላም ለእናንተ ይኹን መቅረዞች!!! አንድ ውስጤን የሚያስጨንቀኝና እንቅልፍ ያሳጣኝ ጥያቄ አለኝ፡፡ ለብዙ ዓመታት እምነቴ ፕሮቴስታንት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. 2010 ላይ ግን ወደ ኦርቶዶክስ ተመልሻለኁ፡፡ ከንስሐ አባቴ ጋርም ተገናኝቻለኁ፡፡ ነገር ግን ኃጢአቴን ስናዘዝ በደፈናው “ከመግደል ውጪ ኹሉንም ሠርቻለኁ” ነው ያልኳቸው፡፡ አኹን ግን “ለምን ኹሉንም በዝርዝር አልነገርኳቸውም? በግልጽ ባለ መናገሬ እግዚአብሔር ይቅር ባይለኝስ? እንዴትስ በድጋሜ ልንገርዎት ልበላቸው?” እያልኩ ቀን በቀን እጨነቃለኁ፡፡ ምን እንዳደርግ ትመክሩኛላችኁ? 
ሳምራዊት ነኝ ከሆላንድ

Tuesday, March 24, 2015

የመስጠትና የመቀበል ስሌት




በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማግሰኞ መጋቢት 15 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
        ውድ የመቅረዝ ዘተዋሕዶ አንባብያን እንዴት አላችኁ? ይኽ ዛሬ የምናቀርብላችኁ ጽሑፍ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ማኅበረ ቅዱሳን መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በኦሎንኮሚ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀው 8ኛው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ላይ የሰበከው ስብከት ነው፡፡ ስብከቱ 44 ደቂቃን የፈጀ በመኾኑ ወደ ጽሑፍ ሲቀየር ትንሽ ረዘም ይላል፡፡ ነገር ግን የሐሳቡ ፍሰት እንዳይቆራረጥ ብዬ በክፍል በክፍል ላቀርበው አልመረጥኩም፡፡ ከዚኽም በተጨማሪ በስብከቱ ውስጥ የሚደጋገሙ ዐረፍተ ነገሮችንና በጉባኤው ላለ ሰው ካልኾነ በቀር ለአንባቢ የማይረዱ ጥቃቅን ሐሳቦችን ከማውጣት ውጪ ምንም የቀነስኩትም የጨመርኩትም ነገር የለም፡፡ ስለ ኹሉም መልካም ንባብ ይኹንላችኁ!!!

Wednesday, March 18, 2015

በተመሳሳይ ኃጢአት እየወደቅኩ ተቸገርኩኝ፡፡ ምን ላድርግ?

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሑደ አምላክ አሜን!!!
        ውድ መቅረዛውያን እንዴት አላችኁ? በዛሬው ጽሑፋችን ከአንባብያን ከተላኩልን ጥያቄዎች አንዱን ካህናትን ጠይቀን መልስ ይዘን መጥተናል፡፡ መልሱን የሚሰጡን በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል እንዲኹም በታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳም የመጻሕፍተ ሐዲሳት የ5ኛ ዓመት ደቀ መዝሙር የኾኑት ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ናቸው፡፡ ለርሳቸው ተናጋሪ አንደበት ለእኛም ሰሚ እዝነ ልቡና ያድለን፡፡ አሜን!!!
ጥያቄ፡- “እንደምን አላችኁ መቅረዞች? እባካችሁ አንድ ኃጢአት በተደጋጋሚ እሠራለሁ፡፡ ንስሐ አባቴ ጋር በተደጋጋሚ ብሔድም ኃጢአቴን መተው አልቻልኩም፡፡ ምን ላድርግ? እባካችሁ ጉልበት የሚኾነኝ ምክር ስጡኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡”

Monday, March 16, 2015

ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ (ደረጃ አራት)





በዲ/ን ሳምሶን ወርቁ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
መታዘዝ
የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፥ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተጓዦች እንዴት ሰነበታችሁ? አራተኛውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ እነሆ በምናባችን ዛሬ መመልከታንን እንቀጥላለን፡፡ አስቀድመን የመጀመሪያውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ጀርባችን ለዓለም በመስጠት ጀምረን፣ ሁለተኛውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ከዓለማዊ መሻት መለየትን አስከትለን፣ በሦስተኛው የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ የሆነውን እንደ እንግዳ መኖርን በባለፉት ጊዜያት ተመልክተናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ዘላዕለይ አራተኛውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ መታዘዝ ሲል ይገልጸዋል፡፡ ይህንንም ሲገልጽ መታዘዝ ማለት የእኔ የምንለውን ሐሳብ፣ ፈቃድ በመተው በምትኩ እኛ ራሳችንን አስገዝተንለታል ለምንለው ለእግዚአብሔር ፈቃድ በመታዘዝ መኖር ማለት ነው፡፡

Thursday, March 12, 2015

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 03 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
     በየዓመቱ መጋቢት 5 የምናከብረው በዓል አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉበት በዓል ነው፡፡ በዚኽ ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በቅዳሴዋም በትምህርቷም ኹሉ እኒኽን ታላቅና ቅዱስ አባት ታነሣለች፤ ታወድሳለች፤ ተጋድሎአቸውንም ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡
ሀገራቸው ንሒሳ (ግብጽ) ሲኾን አባታቸው ስምዖን እናታቸውም አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዓመታት ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ እኛ አንድ ነገርን ለምነን በእኛ አቈጣጠር ካልተመለሰልን ስንት ቀን እንታገሥ ይኾን? ዛሬ በልጅ ምክንያት የፈረሱ ትዳሮች ስንት ናቸው? ለመኾኑ እግዚአብሔርን ስንለምነው እንደምን ባለ ልቡና ነው? ጥያቄአችን ፈጥኖ ላይመለስ ይችላል፡፡ ያልተመለሰው ለምንድነው ብለን ግን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡- “የምንለምነውን የማናገኘው በእምነት ስለማንለምን ነው፤ በእምነት ብንለምንም ፈጥነን ተስፋ ስለምንቆርጥ ነው” ይላል፡፡ ሰውን ብንለምነው እንደዘበዘብነው፣ እንደ ጨቀጨቅነው አድርጎ ሊቈጥረው ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን እንዲኽ አይደለም፡፡ “ለምኑ ታገኙማላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል” ያለን ርሱ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለምና፡፡ የሚያስፈልገን ከኾነ ያለ ጥርጥር ይሰጠናል፡፡ መቼ? ዛሬ ሊኾን ይችላል፤ ነገ ሊኾን ይችላል፤ ወይም እንደ ስምዖንና እንደ አቅሌስያ የዛሬ 30 ዓመት ሊኾን ይችላል፡፡  ጭራሽኑ ላይሰጠንም ይችላል፡፡ አልሰጠንም ማለት ግን ጸሎታችን ምላሽ አላገኘም ማለት አይደለም፡፡ የለመንነው እኛን የሚጎዳን ስለኾነ እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ሲሰጥ ስለ ፍቅሩ፤ ሲነሳም ስለ ፍቅሩ ነውና፡፡

Tuesday, March 10, 2015

ኹለት መንፈሳውያን መጻሕፍት ተመረቁ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ረቡዕ 02 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- “ሰማዕትነት አያምልጣችሁ” እና “ነጽሮተ ሀገር” በሚል ርእስ የተዘጋጁ ኹለት መንፈሳውያን መጻሕፍት የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው አበው ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ሰባክያነ ወንጌል እና የመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ አንባብያን በአጠቃላይ ከ400 በላይ ታዳምያን በተገኙበት ደማቅ መርሐ ግብር ተመረቁ፡፡ “ሰማዕትነት አያምልጣችሁ” የሚል ርእስ የተሰጠው አንደኛው መጽሐፍ በመቅረዝ ዘተዋሕዶ ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ በገ/እግዚአብሔር ኪደ የተተረጐመ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሥራ ሲኾን ኹለተኛው መጽሐፍ ደግሞ በመምህር ዘሪኹን መንግሥቱ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው፡፡ መርሐ ግብሩ በአባ አሥራተ ማርያም ደስታ በጸሎት የተከፈተ ሲኾን ዘማሪት ጽጌ ወቅቱን የተመለከተ ያሬዳዊ መዝሙር አቀረበች፡፡

Wednesday, March 4, 2015

በመጽሐፍ ምረቃ ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ረቡዕ የካቲት 28 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
     ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ውድ የመቅረዝ አንባብያን፡፡ እንደምን ሰነበታችሁ? እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ ቀጣይ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በገ/ጽ/ቅ/ጊ/ቤተ ክርስቲያን (ፒያሳ) ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ዠምሮ ኹለት መጻሕፍት አንድ ላይ ይመረቃሉ፡፡ አንደኛው መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ሲኾን ኹለተኛው መጽሐፍ ደግሞ የዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል ሰብሳቢ በኾኑት በመምህር ዘሪኹን መንግሥቱ የተዘጋጀ ነው፡፡