ያቺ ውብ ጨረቃ በጣም የደመቀች
ውቢቷ ጨረቃ፤
ደም ለበሰች አሉኝ
በኃይል ተጨንቃ፡፡
እርቃኑን ሲያስቀሩት የዓለም ፈጣሪ
ከላይ ተመልክታ ከልቧ አዘነች፤
ይህን አላደርግም ድምቀቴ በሱ ነው
ብላ ራሷን ጣለች፡፡
ደሙ ሲፈስ አይታ፤
ህመም ግርፋቱን እሷም ተመልክታ፤
ጌታ ሲንገላታ፤
አይ አይሆንም አለች
አይኖቿን ጨፈነች፤
የጭንቀቷ ብዛት
እሷም ደም ለበሰች፡፡
ያቺ ውብ ጨረቃ
ለዓለም ብርሃን ልትሰጥ
ብሎ የፈጠራት፤
የዓለም ፈጣሪ አክሊለ ሶኽ አርጎ
መመልከት አቃታት፡፡
ያቺም ጥቅመ ብዙ
የብርሃን እመቤት እመት ፀሐይቱ፤
አላችልም አላት ለዓለም ማሳየት
ህመም ግርፋቱ፤
በጦር መወጋቱ፤
አላችልም አላት አይታ እሱን ማሳየት
ምራቅ መተፋቱ፤
አቅም አጣሁ አለች የዓለም ፈጣሪ
ሲሰቀል ማየቱ፡፡
ያቺ ደማቅ ፀሐይ
በምርምር ሂደት ማንም ያላወቃት፤
አሁን አሉኝ ከፋት፡፡
ጨለመች፤
ጨለመች፤
ጨለመች፤
ይሉኛል አሁን ግብሯን ተወች፡፡
ጌታዋ ሲገረፍ ሲተፋበት አይታ
አይኗን ጨፈነችው፤
ስትሰጥ የነበረው ያን ሁሉ ብርሃኗን
ለዓለም ነፈገችው፡፡
እኔ አላይም አለች የድንግል ሰቆቃ
የዛች ርህርህት እናት፤
ብርሃኗ ብዙ እጥፍ እኔ ታናሽቱ
እንደምን ልቻላት፡፡
አለች አሉኝ ፀሐይ
የድንግል ሃዘናት አልችልም መመልከት፤
ጌታዬ እርቃን ሆኖ ልብሱ ሲቀዳደድ
ዕጣ ሲጣልበት፡፡
ብርሃን ይሁን ያለው የብርሃን ጌታ፤
በቀራንዮ ላይ ታየ ሲንገላታ፡፡
ውሃን የፈጠረ
የባሕራት የወንዞች የአፍላጋት ጌታ፤
ውሃ ጠማኝ ብሎ ሐሞት ቀረበለት
በኃጥአን ተመታ፡፡
እነዚህ ፍጥረታት
ቀን ከሌት የከፈሉ፤
ጌታቸው ሲገረፍ ፤
ህመሙ ሲበዛ መች መቋቋም ቻሉ?
እነዚህ ፍጥረታ ትግብራቸውን ትተው
ከአምላክ ሲወዳጁ፤
እኔ ደካማው ግን
እኔ ባይ ወዳጁ፤
የዘመኔን ኃጢአት
አይኔ ቢጋርደው፤
ጲላጦስ ፊት ቆሜ
ስላለሁ ስቀለው፤
እላለሁ ስቀለው፤
ወየው ወየው ወየው፡፡
ማኅደር ታፈሠ
19/08/08 ከምሽቱ 4፡50
ውቢቷ ጨረቃ፤
ደም ለበሰች አሉኝ
በኃይል ተጨንቃ፡፡
እርቃኑን ሲያስቀሩት የዓለም ፈጣሪ
ከላይ ተመልክታ ከልቧ አዘነች፤
ይህን አላደርግም ድምቀቴ በሱ ነው
ብላ ራሷን ጣለች፡፡
ደሙ ሲፈስ አይታ፤
ህመም ግርፋቱን እሷም ተመልክታ፤
ጌታ ሲንገላታ፤
አይ አይሆንም አለች
አይኖቿን ጨፈነች፤
የጭንቀቷ ብዛት
እሷም ደም ለበሰች፡፡
ያቺ ውብ ጨረቃ
ለዓለም ብርሃን ልትሰጥ
ብሎ የፈጠራት፤
የዓለም ፈጣሪ አክሊለ ሶኽ አርጎ
መመልከት አቃታት፡፡
ያቺም ጥቅመ ብዙ
የብርሃን እመቤት እመት ፀሐይቱ፤
አላችልም አላት ለዓለም ማሳየት
ህመም ግርፋቱ፤
በጦር መወጋቱ፤
አላችልም አላት አይታ እሱን ማሳየት
ምራቅ መተፋቱ፤
አቅም አጣሁ አለች የዓለም ፈጣሪ
ሲሰቀል ማየቱ፡፡
ያቺ ደማቅ ፀሐይ
በምርምር ሂደት ማንም ያላወቃት፤
አሁን አሉኝ ከፋት፡፡
ጨለመች፤
ጨለመች፤
ጨለመች፤
ይሉኛል አሁን ግብሯን ተወች፡፡
ጌታዋ ሲገረፍ ሲተፋበት አይታ
አይኗን ጨፈነችው፤
ስትሰጥ የነበረው ያን ሁሉ ብርሃኗን
ለዓለም ነፈገችው፡፡
እኔ አላይም አለች የድንግል ሰቆቃ
የዛች ርህርህት እናት፤
ብርሃኗ ብዙ እጥፍ እኔ ታናሽቱ
እንደምን ልቻላት፡፡
አለች አሉኝ ፀሐይ
የድንግል ሃዘናት አልችልም መመልከት፤
ጌታዬ እርቃን ሆኖ ልብሱ ሲቀዳደድ
ዕጣ ሲጣልበት፡፡
ብርሃን ይሁን ያለው የብርሃን ጌታ፤
በቀራንዮ ላይ ታየ ሲንገላታ፡፡
ውሃን የፈጠረ
የባሕራት የወንዞች የአፍላጋት ጌታ፤
ውሃ ጠማኝ ብሎ ሐሞት ቀረበለት
በኃጥአን ተመታ፡፡
እነዚህ ፍጥረታት
ቀን ከሌት የከፈሉ፤
ጌታቸው ሲገረፍ ፤
ህመሙ ሲበዛ መች መቋቋም ቻሉ?
እነዚህ ፍጥረታ ትግብራቸውን ትተው
ከአምላክ ሲወዳጁ፤
እኔ ደካማው ግን
እኔ ባይ ወዳጁ፤
የዘመኔን ኃጢአት
አይኔ ቢጋርደው፤
ጲላጦስ ፊት ቆሜ
ስላለሁ ስቀለው፤
እላለሁ ስቀለው፤
ወየው ወየው ወየው፡፡
ማኅደር ታፈሠ
19/08/08 ከምሽቱ 4፡50
ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡
ReplyDelete