Showing posts with label ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ. Show all posts
Showing posts with label ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ. Show all posts

Monday, October 8, 2012

ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ


   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

የዚህ ትምህርት መሠረታዊ ዓላማ ክርስቲያኖች ከጌታችንና ከእመቤታችን ስደት በረከት ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ቀዳማዊ አዳም የማይበላ በልቶ በራሱና በልጆቹ የሞት ሞት ተፈረደበት፤ ጸጋ እግዚአብሔር ጎደለበት፤ የሚሠዋው መሥዋዕት የሚጸልየው ጸሎት ግዳጅ የማይፈጽም ሆነበት፡፡ ምድር ከእርሱ የተነሣ እሾክና አሜከላ አበቀለችበት፡፡ 

ሆኖም (አዳም) ምንም ባልበደለው ሰይጣን እንዲሁ ቢሞትም የተበደለው አምላኩ ግን እንዲሁ ሕይወትን ይሰጠው ዘንድ ወደደ፡፡ (አዳም) አምላክ መሆንን ሽቶ ነበርና ይህን ይሰጠው ዘንድ (አምላክ) ዳግማይ አዳም ይሆንለት ዘንድ ወደደ፤ አስቀድሞ ከነበረው ክብር በላይ ሌላ ክብር ይጨምርለት ዘንድ ፈቀደ፡፡ ጊዜው ሲደርስም አካላዊ ቃል ንጹሕ የሆነ ባሕርዩን (የእመቤታችን ሥጋና ነፍስ) ነሥቶ ዝቅ ያለውን ከፍ ያደርገው ዘንድ ዝቅ አለለት፤ የጸጋ ልብሱን ይመልስለት ዘንድ የማይዳሰስ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለት፤ ወደ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ በርካሽ ቦታ ያውም በግርግም ተወለደለት፡፡

FeedBurner FeedCount