Friday, July 25, 2014

††† መቅረዝ ዘተዋሕዶ - የውዳሴ ማብራርያ መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ትውላለች †††


መቅረዝ ዘተዋሕዶ ከዚኽ በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ነው፡-
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳይለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንዲደርስ በማሰብ መዘጋጀቷ፤
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉ” የሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውን መለየቷ፤
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያ መያዟ፤
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድ መክፈቷ፡

በመኾኑም ላለፉት ዐራት ዓመታት በድረ ገጽ መልክ ስታገለግላችኁ የነበረችውን መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አኹን ደግሞ ለኹሉም ምዕመናን ትዳረስ ዘንድ በመጽሐፍ መልክ መምጣቷን ስታበሥር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው፡፡ ርስዎም ይኽችን መጽሐፍ በመግዛት ይጠቀሙ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
በዚኹ አጋጣሚ የማሳተሚያ ወጪዋን ሙሉ ለሙሉ በመሸፈን ከጐኔ ላልተለያችኁኝ የመቅረዝ ዘተዋሕዶ ወዳጆች እናንተን የማመሰግንበት ምንም ቃላት የለኝም፡፡ ኹሉን ማድረግ የማይሳነው እግዚአብሔር ዋጋቸኁን በሰማያት ያቈይላችኁ፡፡
መጽሐፏን ማከፋፈል ወይም ማግኘት የምትፈልጉ፡-
• በስልክ ቁጥር 09 12 07 45 75
• በፖ.ሳ.ቁ. 8665 አ.አ.
• በእ-ጦማር gebregzabher@gmail.com መገናኘት እንችላን!!!
— with Mahder Tafesse and 29 others.

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount