በታምራት ፍሰሓ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር ፪
ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- ኦርቶዶክሳዊት እምነታችን በብዙ
መስክ (በቅዳሴ ፡ በማህሌት ፡ በሰአታት ፡
በሰርክ ጉባኤያት ፡
በበዓላት ዝግጅቶች) በልዩ
ስርአት ና ወጥነት ሐዋርያዊ መሰረተ እምነቷን ለምእመናን ስታስተላልፍ
ቆይታለች ፡ አሁንም በማስተላለፍ ላይ ትገኛለች፤ በቅዳሴው ለተካፈለ ፡
በማህሌቱም ለተሳተፈ ፡
በሰአታቱም ለተገኘ ፡
በሰርክ ጉባኤውም ላልቀረ ይህ እሙን ነው፡፡ ነገር ግን ስንቶቻችን በነዚህ ተገኘን? ካልተገኘንስ እንደምን እምነታችንን
ልናውቅ ፡ በእምነታችንስ ልንፀና ይቻለናል?
ብዙወቻችን ደግሞ
የቤተክርስቲያን ታላላቅ በዓላትን (ደመራ ፡ ጥምቀት) መሰረት በማድረግ ተገኝተን እናከብራለን ፡ ይህም
በጣም ብዙ ኦርቶዶክሳዊ
በአንድነት የሚገናኙባቸው
ክስተቶች ቢሆኑም ፡
ነገር ግን እኒህ ልዩ
በዓላት እንደመሆናቸው
የራሳቸው የሆነ የአከባበር ስርአትና ይዘት ያላቸው በመሆኑ በዚህ ጊዜ
ለሚገኙ ምእመናን የሚገባውን ያህል ትምህርት ሰጥተው የሚያልፉ አይደለም ፡
ይልቅስ በነዚህ በዓላት ጥቂት ከመዘመርና በዓሉን የመታዘብ ያክል ከተመለከትን በኅላ ወደቤታችንም
ሆነ ወደሌሎች ጉዳዮች የምንመለስ ብዙወች ነን፡፡ ስለዚህም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በአንድነት ተሰባስበን የቤተክርስቲያናችንን
ስብከቷን ፡ ዝማሬዋንም ሆነ ልዩ ልዩ
ሃሳቦቿን የምንረዳባቸው
፡ የምንሳተፍባቸውና የምንወያይባቸው
መድረኮች የሉንም፡፡