በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 7 ቀን፣
2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሥጋችን
በደዌ
ተመትቶ
መከራ
በጸናብን
ጊዜ፣
የኢዮብን
ሥቃይ
ማሰብ
አቅቶን
በደጅ
ተንቀን
በወደቅን
ጊዜ፣
የምሬታችን
ብዛት
በአህዛብ
ዘንድ
ስድብ
ሲሆንብን፣
በደጅህ
ወድቀን
የሚያነሳን
ባጣን
ጊዜ፣
የወለዱን
እንኳን
እኛን
እስከመጨረሻው
መሸከም
ከብዷቸው
በጣሉን
ጊዜ፣
ሊሰሙን
ያልወደዱ
ነገስታት
ሊጎበኙን
ያልፈቀዱ
ካሕናት
በተሠበሰቡ
ጊዜ፣
በቁስላችን
ላይ
ዘይትን
በጥዝጣዜያችን
ላይ
መድኃኒትን
የሚያፈሱልንን
ባጣናቸው
ጊዜ፣
አንተ
ሳንጠራህ
መጥተህ
ሳንጠይቅህ
ወደህ
ሳንመካብህ
መመኪያችን
ሆነኸን
ከሞት
ጥላ
በአባታዊ
አጠራርህ
ልጆቼ
ብለህ
ጠርተህ
“ልጆቼ
መዳን
ትወዳላችሁን?”
ብለህ
እንደ
ታናሽ
አስፈቅደህ
መንጻትን
በፈቀድን
ጊዜ
ከደዌያችን
ሁሉ
ጎንበስ
ብለህ
አጠብከን፡፡
ስለዚህም
ማንም
ሊሰጠን
ያልፈቀደውን
ሰላም
ይልቁንም
ማንም
የሌለውን
ሰላም
ሰጠኸን::
በዚህ
ሰላም
ለሁላችሁ
ሰላም
ይሁንላችሁ!