(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 13፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን!!!
የሃይማኖት አዠማመርና ዕድገት
የተለያዩ ሰብአ ዓለም (የዚኽ ዓለም ሰዎች) የሃይማኖት አመጣጥን
በተመለከተ የተለያየ ዓይነት አመለካከት ቢኖራቸውም፥ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ሃይማኖት ገና ከፍጥረት መዠመሪያ (ከዓለመ መላዕክት)
ዠምሮ የነበረ መለኮታዊ ስጦታ ነው ብለን እናምናለን /ሐዋ.17፡26/፡፡ የመዠመሪያዎቹ ምእመናንም ቅዱሳን መላዕክት ናቸው፡፡ ይኽ
እንዴት እንደኾነም በሥነ ፍጥረት ትምህርታችን የምንመለስበት ይኾናል፡፡
ከቅዱሳን መላዕክት በኋላ ይኽቺው
ነቅዕ፣ ኑፋቄ የሌለባት ንጽሕት ሃይማኖት አዳምና ሔዋን በተፈጠሩ በ40 እና በ80 ቀናቸው ተቀብለዋታል፡፡