በዲ/ን ሳምሶን ወርቁ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 17 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በክርስትና
ሕይወት ውስጥ ምዕመናን ስለመንፈሳዊነት ያላቸው ግንዛቤ ብዙ ጊዜ ያልተሟላ አንዳንዴ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊነት ብለው የሚያስቡት
መንፈሳዊነት ያልሆነውን ሆኖ ይገኛል፡፡ ከዚህ የተነሣ ብዙዎች መንፈሳዊያን ናቸው ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች ሕይወት ተመልክተው
መንፈሳዊነት እንዲህ ከሆነ ይቅርብኝ እስከማለት ይደርሳሉ፡፡ ነገር ግን መንፈሳዊነት ትርጉሙ ዓላማው ምስጢሩ የረቀቀ የጠለቀ ነው፡፡