በዲ/ን
ሳምሶን ወርቁ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማክሰኞ መጋቢት
8 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
መታዘዝ
የተከበራችሁ
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፥ የመንግሥተ እግዚአብሔር ተጓዦች እንዴት ሰነበታችሁ? አራተኛውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ እነሆ በምናባችን
ዛሬ መመልከታንን እንቀጥላለን፡፡ አስቀድመን የመጀመሪያውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ጀርባችን ለዓለም በመስጠት ጀምረን፣ ሁለተኛውን
የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ ከዓለማዊ መሻት መለየትን አስከትለን፣ በሦስተኛው የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ የሆነውን እንደ እንግዳ መኖርን
በባለፉት ጊዜያት ተመልክተናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ዘላዕለይ አራተኛውን የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ መታዘዝ ሲል ይገልጸዋል፡፡ ይህንንም
ሲገልጽ መታዘዝ ማለት የእኔ የምንለውን ሐሳብ፣ ፈቃድ በመተው በምትኩ እኛ ራሳችንን አስገዝተንለታል ለምንለው ለእግዚአብሔር ፈቃድ
በመታዘዝ መኖር ማለት ነው፡፡