(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 5 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡-
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
“ሃይማኖት” ማለት አምነ፣ አመነ ከሚል የግእዝ ግሥ የወጣ ሲኾን መዝገበ ቃላታዊ ትርጓሜውም “ማመን፣ መታመን” ማለት ነው፡፡ በምሥጢራዊው ትርጕሙ ግን “ሃይማኖት” ማለት ፍጥረትን ኹሉ ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣ አንድ እግዚአብሔር እንዳለ፣ ለሚታየውም ለማይታየውም ፍጥረት ሠራዒውና መጋቢው ርሱ ብቻ እንደኾነ፣ ልዩ ሦስትነት እንዳለው፣ በዚኽ አለ በዚኽ የለም የማይባል ምሉዕ በኵለሄ እንደኾነ፣ … ማመን መታመን ማለት ነው፡፡