Showing posts with label የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (የመጨረሻው ክፍል). Show all posts
Showing posts with label የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (የመጨረሻው ክፍል). Show all posts

Friday, December 19, 2014

የንስሐ ልጆቼን እንዴት ላገልግል? (የመጨረሻው ክፍል)

በዳዊት አብርሃም
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ቅዳሜ ታኅሳስ 11 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የጽሑፉ ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት፥ የግንቦት 2005 ዓ.ም. እትም ነው፡፡
ኃጢአትን በመናዘዝ ውስጥ የሚገኝ ፈውስ
ከኃጢአት እስራት በንስሐ ለመፈታት ፈልጐ ወደ ካህኑ የሚቀርብ ተነሳሒ የሚታይበትና ከዚያም በሒደት አልፎበት በመጨረሻ የሚደርስበት የመንፈስና የሥነ ልቡና ኹኔታ አለ፡፡ ይኽንን ኹኔታ ቀሲስ ፋሲል ታደሰ እንደሚከተለው ይገልፁታል፡፡
ደረጃ አንድ
ተነሳሒው ለመዠመሪያ ጊዜ ሲመጣ የተረበሸ ኹኔታ ፊቱ ላይ ይነበባል፡፡ ቁጣ ቁጣ የሚለው የዘለፋና ወቀሳ የሚያበዛ ለራሱ የሰጠውን ዝቅተኛ ግምትና ውስጡ ያደረውን ታላቅ ተስፋ መቁረጥ ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ኹኔታዎች ከገጽታው ይነበባል፤ ካንደበቱ ይደመጣል፡፡

FeedBurner FeedCount