Showing posts with label የንስሐ አባቴ ኃጢአቴን ቀለል አድርገው ስለሚነግሩኝ ንስሐ ለመግባት እቸገራለሁ፡፡ ምን ላድርግ?. Show all posts
Showing posts with label የንስሐ አባቴ ኃጢአቴን ቀለል አድርገው ስለሚነግሩኝ ንስሐ ለመግባት እቸገራለሁ፡፡ ምን ላድርግ?. Show all posts

Thursday, July 2, 2015

የንስሐ አባቴ ኃጢአቴን ቀለል አድርገው ስለሚነግሩኝ ንስሐ ለመግባት እቸገራለሁ፡፡ ምን ላድርግ?



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 25 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ውድ መቅረዛውያን እንዴት አላችሁ? ዛሬም ከአንባብያን ከተላኩልኝ ጥያቄዎች መካከል አንዱን መርጬ በአበው ካህናት የተሰጠውን ምላሽ ይዤላችሁ ቀርቢያለሁ፡፡ ዛሬም መልሱን የሚሰጡን በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል እንዲሁም መጋቤ አእላፍ ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ናቸው፡፡ ለአባታችን ተናጋሪ አንደበት ለእኛም ሰሚ እዝነ ልቡና ያድለን፡፡ አሜን!!!
ጥያቄ፡-  “ውድ የመቅረዞች አዘጋጆች! እንዴት አላችሁ? የመቅረዝ ዘተዋሕዶ አንባቢ ነኝ፡፡ ከምእመናን የምታስተናግዱት ጥያቄ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እኔም ከንስሐ አባት ጋር የተያያዘ ጥያቄ አለኝ፡፡ ለካህናት እንዲህ አደረግኩ ብዬ ስናገር፡- ‘ምንም ችግር የለውም፡፡ ይህቺ’ማ ምን አላት?’ እያሉ በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ሌላውን ለመናገር ቸገረኝ፡፡ ምን ላድርግ?”
አንዳርግ ነኝ ከቺካጎ

FeedBurner FeedCount