Showing posts with label የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ት/ቤት. Show all posts
Showing posts with label የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ት/ቤት. Show all posts

Friday, July 31, 2015

የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ትናንት፣ ዛሬና ነገ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 24 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ ተቋም ከተመሠረተ ከ82 ዓመታት በላይ ኾኖታል፡፡ በእነዚህ አገልግሎት ዘመናቱም በርካታ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት፣ አባቶች መምህራንና ካህናትን አፍርቷል፡፡ ማሠልጠኛው ጥንታዊው የሀገራችን ቋንቋና ፊደል ግእዝና ትምህርቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ለትውልድም እንዲተላለፍ በማድረግ በኩል ታላቅ ድርሻ አለው፡፡ የቤተክርስቲያን አባቶችና ምእመናን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን አለኝታና ቅርስ መኾኑን በኩራት የሚናገሩለት ተቋም ነው፡፡
ይኼው ማሠልጠኛ በረጅም ጊዜ አገልግሎት ለቤተክርስቲያንም ኾነ ለሀገር ከፍተኛ አገልግሎትና ጥቅም የሰጠ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዚህን ት/ቤት ትናንት የነበረውን ገጽታ ዛሬ ያለበትንና ወደፊት የሚጠበቅበትን በዚህች አነስተኛ ጽሑፍ እንዳስሳለን፡፡

FeedBurner FeedCount