ገ/እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ኅዳር ፲፬ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
“ጾም”
በፊደላዊ ትርጕሙ- “ጾመ”፣ “ተወ”፣ “ታቀበ”፣ “ታረመ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ነው፡፡ የቃሉ ፍቺ ምግብ መተው፣ መከልከል፣
መታቀብ፣ መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ቃሉ በዕብራይስጥና በሱርስት ቋንቋዎች “ጻም” ሲባል በዐረብኛ ደግሞ “ጻመ” ይባላል፡፡ ስለዚኽ
ጾም ማለት ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች በቤተ ክርስቲያን የሥርዓት መጻሕፍት ከተወሰነው ጊዜ ሳያጓድሉ መከልከል ወይም
ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ሰውነት ከሚያስፈልገው ነገሮች ሁሉ መወሰን (መታቀብ) ማለት ነው፡፡