Monday, August 4, 2014

መቅረዝ ዘተዋሕዶ - የውዳሴ ማብራርያ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለች



መቅረዝ ዘተዋሕዶ ከዚኽ በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም፡-
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳትለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንድትደርስ በማሰብመዘጋጀቷ፤
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉየሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውንመለየቷ፤
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራርያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያመያዟ፤
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድመክፈቷ ነው፡፡

በመኾኑም ላለፉት ዐራት ዓመታት በድረ ገጽ መልክ ስታገለግላችኁ የነበረችውን መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አኹን ደግሞ ለኹሉም ምዕመናን ትዳረስ ዘንድ በመጽሐፍ መልክ መምጣቷን ስታበሥር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው፡፡ ርስዎም ይኽችን መጽሐፍ በመግዛት ነፍስዎን ይመግቧት ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡


በዚኹ አጋጣሚ የማሳተሚያ ወጪዋን ሙሉ ለሙሉ በመሸፈን ከጐኔ ላልተለያችኁኝ የመቅረዝ ዘተዋሕዶ ወዳጆች እናንተን የማመሰግንበት ምንም ቃላት የለኝም፡፡ ኹሉን ማድረግ የማይሳነው እግዚአብሔር ዋጋቸኁን በሰማያት ያቈይላችኁ፡፡

መጽሐፏን ማከፋፈል ወይም ማግኘት የምትፈልጉ፡-
በስልክ ቁጥር 09 12 07 45 75
በፖ... 8665 ..
 በእ-ጦማር gebregzabher@gmail.com መገናኘት እንችላን!!!

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount