መቅረዝ ዘተዋሕዶ ከዚኽ በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም፡- 
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳትለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንድትደርስ በማሰብ በመዘጋጀቷ፤ 
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉ” የሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውን በመለየቷ፤ 
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራርያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያ በመያዟ፤ 
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድ በመክፈቷ ነው፡፡
