በክፍለ ሥላሴ
(መቅረዝ
ዘተዋሕዶ፣ ጳጉሜ 1 ቀን፣ 2005 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ
ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ
አሜን፡፡
መግቢያ
ቅዱስ መጽሐፋችን «የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ
ተፈትናለች፣ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው፡፡ እንዳይዘልፉህ ደግሞም ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር» (ምሳ.30÷6) ይላል፡፡ ሰማያዊውን ወንጌል ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል መንፈሳውያን
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል
መሪነት መረመሩት፣ አመኑት አልፈውም ታመኑበት የጠላትን የክህደት ጦር ይመክቱበት ዘንድ ጋሻ ሆናቸው፡፡ ፈቃዳቸው እና የልባቸውም ሃሳብ የሚመራቸው ግን
በገዛ መንገዳቸው ቃሉን ፈትነው የተከደነውን ሊገልጡ የተሰወረውን ሊያወጡ ቢባዝኑ ጥርጣሬን ጸንሰው ክህደትን ይወልዳሉ፣ ሀሰትን ጨምረው ተዘልፈው ይጠፋሉ፡፡ «ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉት ነው» (1ቆሮ
4÷3)፡፡