በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
(መዝረቅ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 16 ቀን፣
2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኹለተኛው በይሁዳ ነው!
ይሁዳ
የኢየሩሳሌም አውራጃው ነው፡፡ የይሁዳ አውራጃ ዋና ከተማም ኢየሩሳሌም ነች፡፡ ከኢየሩሳሌም ይሁዳ ይከፋል፤ ከሰማርያ ግን ይሻላል፡፡
ምክንያቱም ኢየሩሳሌም ዋና ከተማዋ ነች፣ ጌታም የተወለደው በይሁዳ አውራጃ በቤተ ልሔም ነው፡፡ የተሰቀለው፣ የሞተው፣ የተቀበረው፣
ያረገው፣ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከው በኢየሩሳሌም ከተማ ነው፡፡ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ነገር በይሁዳ አውራጃ የተሻለ ይወራል፤
ይነገራል፡፡ የሚያውቁት ዘመድ ይኖራል፡፡ የሐዋርያትና የይሁዳ ቋንቋ ተመሳሳይ ነው፡፡ የይሁዳ ባሕልና የኢየሩሳሌም ባሕል ተመሳሳይ
ነው፡፡ ከሰማርያ ቢሻልም ከኢየሩሳሌም ግን ይከፋል፡፡