ከጌታችን ስቅለት በፊት መስቀል መቅጫ ነበር፡፡ ሰውን በመስቀል መስቀል የጀመሩት ፋርሳውያን ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የሚባል የመሬት አምላክ ስለበራቸው እርሱን ላለማርከስ ብለው ወንጀለኛውን ሁሉ ከመሬት ከፍ አድርገው ሰቅለው ይቀጡት ነበር፡፡ በኋላም ይህ አድራጎት በሮማውያን ግዛት ሁሉ ሕግ ሆነ፡፡
በኦሪቱ ሥርዓትም በመስቀል የሚቀጡ ርጉማን ውጉዛን ነበሩ፡፡ ከጌታችን ስቅለት በኋላ ግን የነጻነታችን አርማ የድል ምልክታችን ሆነ፡፡ ክርስቶስ ይህን መስቀል ዙፋኑ አድርጎ ሰላምን እኩልነትን አድርጓልና፡፡ ስለዚህ ካሉን ነገሮች ሁሉ መስቀል የላቀ ክብር አለው፡፡