(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ ፳፭ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
2. ተነሥተናል
ሐዋርያው፡-
“ሞታችኋልና” ብሎ አላቆመም፤ ጨምሮም፡- “እንግዲኽ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችኁ” በማለት እንደተነሣንም ነገረን
እንጂ፡፡ በጥምቀት ውኃ ሞቱን በሚመስል ሞት ስንሞት፥ አሮጌው ሰውነታችን እንደ ግብጻውያን ተቀብሮ ቀርቷል፡፡ አዲሱ
ሰውነታችን ግን እስራኤላውያን ባሕሩ ተከፍሎላቸው እንደተሻገሩ ተሻግሯል (ተነሥቷል)፡፡ ብልየት
ያለበት የቀዳማዊ አዳም ሰውነታችን በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተቀብሮ አዲሱ ሰውነታችን ሕይወትን አግኝቶ ተነሥቷል፡፡
መሬታዊው ሰዋችን ሞቶ ሰማያዊው ሰዋችንን ለብሰን መንፈሳውያን ኾነናል፡፡ ወደ ጥንተ ተፈጥሯችን ተመልሰናል፡፡