(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ግንቦት ፬ ቀን፣
፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እስከ ፍጻሜ
ድረስ በዚኽ በተቀመጥንበት ስፍራችን የምንቈይ ከኾነ ክርስቶስ በክብር በሚገለጥበት ወራት በክብር እንገለጣለን፡፡ ከተቀመጥንበት
ሰማያዊ ስፍራችን ለቅቀን የምንነሣ ከኾነ ግን የምንገለጠው ከክርስቶስ ጋር በክብር አይደለም፤ የዲብሎስን መልክ ይዘን በሐሳር ነው
እንጂ፡፡ ስለዚኽ አኹን ከዚያ ስፍራ ለቅቆ መኖር የእኛ መገለጫ አይደለም፡፡ ይኽ ሕይወት ሌላ፣ ያም ሕይወት ሌላ ነውና፡፡ ክርስቶስ
አኹን አልተገለጠም፡፡ የእኛም ሕይወት ገና አልተገለጠም፡፡ ስለዚኽ በክብር እስክንገለጥ ድረስ እዚያ ልንቈይ ያስፈልጋል፡፡ መቼ
ነው ታድያ የምንገለጠው? ሕይወታችን ክርስቶስ በክብር ሲገለጥ፤ ዳግም ሲመጣ፡፡ እርሱ ሲገለጥ ሕይወታችን ይገለጣል፤ ክብራችን ይገለጣል፤
ደስታችን ይገለጣል፡፡