(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 12 ቀን፣
2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ልጆች እንደምን ከረማችኁ? የዕረፍት ጊዜአችኁ
እንዴት አለፈ? መልካም ልጆች፡፡ እንግዲኽ ዘመነ ማርቆስ አልፎ አኹን ዘመነ ሉቃስ ገብተናል፡፡ ለአዲሱ ዓመት ያደረሰንን አምላክ
እያመሰገንን በዚኽ ዓመት ደግሞ ጊዜያችንን በአግባቡ ተጠቅመን፣ በትምህርታችንም በርትተን ለጥሩ ውጤት መብቃት አለብን እሺ፡፡ ምክንያቱም
ጊዜውን በአግባቡ የማይጠቀም ልጅ መጨረሻው አያምርም እሺ ልጆች፡፡ ስለዚኽ ጊዜአችንን በአግባቡ መጠቀም አለብን፡፡ ለዚኽም እግዚአብሔር
ይርዳን፡፡