(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 03 ቀን፣
2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የእግዚአብሔር ልጆች እንደምን ሰነበታችኁ? ደኅና
ናችኁ? ትምህርት እንዴት ነው? ጐበዞች፡፡
ባለፈው ጊዜ ስለ ምን እንደተማርን ታስታውሳላችኁ
ልጆች? ጐበዞች፡፡ የተማማርነው ስለ ሥነ ፍጥረት ነው አይደል? እስኪ ካስታወሳችኁ አዳምና ሔዋን መቼ ተፈጠሩ ነበር ያልነው? ጐበዞች፡፡
ልክ ናችኁ፡፡ ዓርብ ነበር የተፈጠሩት፡፡ ዛሬ ደግሞ ስለ አዳምና ስለ ሔዋን ታሪክ እነግራችኋለኁ፡፡ እናንተም ለመስማት ዝግጁ ናችኁ
አይደል? ጐበዞች፡፡