(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 23 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ከኹሉም በፊት አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ማወቅ ያለበት
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከኹሉም በፊት ስለ ነገረ ቤተ ክርስቲያን፣
ስለ ቅዱስ ትውፊት፣ ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት የአተረጓጐም ስልት፣ ስለ ዶግማ እና ስለ ቀኖና በጥቂቱም ቢኾን ማወቅ አለበት፡፡ አስቀድሞ
ከእነዚኽ መሠረታውያን ትምህርቶች ጋር የተዋወቀ ክርስቲያን በትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ) ውስጥ ለሚኖረው ትምህርት መሠረትን
ይይዛል፡፡ የእነዚኽን ጽንሰ ሐሳብ ያልተረዳ እንደኾነ ግን ጭራሽኑ የክርስትናን ጽንሰ ሐሳብም ሊስተው ይችላል፡፡ የብዙዎች
ከቤተ ክርስቲያን መጥፋትም በአንድም ይኹን በሌላ መልኩ የእነዚኽ ኦርቶዶክሳዊ ጽንሰ ሐሳቦች የዕውቀት ማነስ ነው፡፡ ኹሉንም አንድ
በአንድ የምንመለከታቸው ሲኾን ለዛሬ ከነገረ ቤተ ክርስቲያን እንዠምራለን፡፡