(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ነሐሴ 21 ቀን፣
2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የሰኞ
(ሠኞ) ፍጥረት
ሰኞ የሚለው
ቃል “ሰነየ - ሰኑይ” ከሚል የግእዝ ቃል የተገኘ ሲኾን፥ ትርጓሜውም መሰነይ፣ ኹለት ማድረግ፣ ኹለተኛ ዕለት ማለት ነው፤ ሥነ
ፍጥረትን ለመፍጠር ኹለተኛ ቀን ነውና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሠኑይ ማለት ሠነየ፣ ሠናይ፣ አማረ፣ ተዋበ፣ በጌጥ በመልክ ደስ አሰኘ
ማለት ነው፤ ይኸውም በዚህ ዕለት ብርሃን ስለ ተፈጠረ ነው፡፡
ለሰኞ አጥቢያ
በጊዜ ሠርክ (የመጀመሪያው ሰዓተ ሌሊት) እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ “ብዢ ተባዢ፤ ስፊ ተስፋፊ” ብሏት የነበረችው ውኃ ከምድር
ጀምራ እስከ ኤረር ድረስ መልታ ነበር፡፡ በዚሁ ዕለት ማለትም በዕለተ ሰኑይም፥ ጠፈርን ፈጠረ /ዘፍ.1፡6-9/፡፡ እግዚአብሔር
ጠፈርን በፈጠረ ጊዜም በዓለም መልቶ የነበረው ውኃ በአራት ተከፍሏል፡-
ü የምናየው ሰማይ (ጠፈር) (ሥዕለ ማይ)፣
ü ከጠፈር
በላይ የተሰቀለው ሐኖስ፣
ü ለምድር
ምንጣፍ የኾነ ውኃና፣
ü በምድር
ዙርያ እንደ መቀነት የተጠመጠመው ውኃ (ውቅያኖስ) ተብሎ፡፡ በምድር ላይ የምናያቸው ውኆች በምድር ዙርያ ከተጠመጠመው ከዚህ ውቅያኖስ
የቀሩ እንጥፍጣፊ ናቸው፡፡