በዲያቆን ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 11 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኆኅተ ብርሃን ማለት የብርሃን
ደጅ፣ የብርሃን መውጫ ማለት ነው፡፡ አማናዊውን ብርሃን ክርስቶስን ስላስገኘች ኆኅተ ብርሃን የተባለች እመቤታችን ድንግል
ማርያም ናት፡፡ በዚህ ጽሑፍ ብርሃን በቤተ ክርስቲያን አነጋገር ምን እንደ ሆነ እመቤታችን ኆኅተ ብርሃን የመባሏን ምስጢር
እግዚአብሔር አምላክ በገለጠልን መጠን እንመለከታለን፡፡