በዲ/ን
ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 29
ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የኦሪት ሰንኮፍን ከእኛ ያራቅህልን፣
በሚደነቅ አጠራር ከጨለማ ጠርተህ የዳግም ልደትን የሠጠኸን፣ ሰውነታችን ሳይሆን ነፍሳችን የምትጠራበትን ሕጽበት ምሥጢር የገለጥክልን፣ በሌሊት ጨለማ ሕይወታችን ወደ አንተ
እንገሰግሳለን፤ አንተም የጽድቅን የእውነትን ነገር ትገልጥልናለህ:: ከዚያም እውነትህን መመስከር እንጀምራለን:: በመጨረሻም ማንም በሌለበት
ወቅት እንኳን ከመስቀልህ ስር ቅዱስ ሥጋህን
እንገንዝ ዘንድ እንደ ኒቆዲሞስ
ያለፍርሃት በጽድቅና በእውነት እንኖራለን:: ምክንያቱም በአንተ መኖር ያለውን ሰላም ከአይሁድ
ተለይተን አይተናልና:: ይህ ሰላምህ ሁልጊዜ አብሮን ይኖር ዘንድ
ፈቃድህ ይሁን::