Showing posts with label አላዋቂ የያዘው መሣሪያ. Show all posts
Showing posts with label አላዋቂ የያዘው መሣሪያ. Show all posts

Friday, October 18, 2013

አላዋቂ የያዘው መሣሪያ

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ጥቅምት ፱ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም.፤ የጽሑፉ ምንጭ፡ አዲስ ጉዳይ መጽሔት፣ ቅጽ 7፣ ቁ.183፣ መስከረም 18 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- የአምላክህ የእግዚአብሔር ቍጣ እንዳይነድድብህ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ፥ በዙሪያችሁ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተሉ” /ዘዳ.6፡15/ ተብሎ እንደተጻፈው እንኳን ሰው እግዚአብሔርም ይቆጣል፡፡ እግዚአብሔር የሚቆጣ መሆኑንና ተቆጥቶም የሚቀጣ መሆኑን ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች አሉ፡፡ “ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ” /መዝ.18፡8/፤የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤” /ኢሳ.5፡25/ የሚሉትን የመሰሉ በመቶዎች የሚቈጠሩ ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናገኛለን፡፡ እንዲሁም ከቅዱሳን ሰዎች ደግሞ ከታላቁ ነቢይ ከሙሴ ጀምሮ ያሉ ነቢያት ሐዋርያትና አበውም ሁሉ የሚቈጡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጳውሎስ ችሎት ፊት ቀርቦ እየተናገረ ባለበት ሰዓት ሊቀ ካህናቱ አፉን እንዲመቱት ሲያዝ፡- “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳ፥ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው፤ አንተ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን?”/ሐዋ.23፡3/ ሲል በቁጣ ቃል ተናግሮ ነበር፡፡ ስለዚህ ቁጣ በሁላችንም ሊገኝ የሚችልና በራሱም ከተፈጥሮአችን ጋር የሚቃረን ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡

FeedBurner FeedCount