Showing posts with label ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነውን? - ክፍል ፫ -. Show all posts
Showing posts with label ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነውን? - ክፍል ፫ -. Show all posts

Friday, July 26, 2013

ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነውን? - ክፍል ፫ -

በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)፡ ውድ ጠያቂያችን! እንደምን ሰነበቱ? ዳግም እንድንገናኝ፣ መንፈሳዊ ጭውውትም እንድናደርግ የፈቀደልን ለቸርነቱ ስፋት ለፍቅሩም ልኬት የሌለው ደግ ፈጣሪያችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰገነ ይኹን፤ አሜን፡፡ እነሆ ለዛሬ ደግሞ ብዙ ስስ ልብ ያላቸው ወገኖች (በተለይም የይሖዋ ምሥክሮችና ሙስሊሞች) ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ፍጡር ነው” ለማለት ከሚጠቅስዋቸው ቃላተ መጻሕፍት ቀዳሚውን ይዘን ቀርበናል፡፡ እርሱም “እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ” /ምሳ.፰፡፳፪/ የሚለው ነው፡፡ እንኪያስ እኛም ከአማናዊው መርከብ እንሳፈርና ከሊቃውንቱ ጋር ሆነን የምሥጢሩን ጽዋዕ እንቅዳ፤ በጥርጣሬ ፀሐይ ደርቆ የተጠማው ልቦናችንም ከማየ ሕይወት እናጠጣው፡፡

FeedBurner FeedCount