በእግረ ሕሊናችሁ ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ 1010 ኪ/ሜ ልውሰዳችሁ፡፡
የጠቀስኩላችሁን ያህል ርቀት ስትጓዙ ዓድዋ ከተማ ትደርሳላችሁ፡፡ ዓድዋ ማለት “ኦድዋ” ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም
ከበብዋት ማለት ነው፡፡ ከተማዋ ይህን ስም ያገኘችው ዙርያዋ በተስዓቱ ቅዱሳን ገዳማት የተከበበች ስለሆነ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አጠገብዋም ዓዲ አቡን - የአቡን ሀገር የምትባል ሌላ ከተማ
አለች፡፡ እዚያ አከባቢ ብቻ የሚበቅል ቲማቲም መሰል አትክልት አለ፡፡ ስሙም “ጸብሒ አቡን” ይባላል፡፡ የአቡን ወጥ እንደማለት
ነው፡፡