Showing posts with label “ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ” - የዮሐንስ ወንጌል የ48ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.13፡1-19). Show all posts
Showing posts with label “ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ” - የዮሐንስ ወንጌል የ48ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.13፡1-19). Show all posts

Wednesday, September 4, 2013

“ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ” - የዮሐንስ ወንጌል የ48ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.13፡1-19)

ገ/እግዚአብሔር ኪደ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ነሐሴ 29 ቀን፥ 2005 ዓ.ም.)፡- የነገረ መለኮት ሊቃውንት እንደሚያስተምሩት ከዚህ ከ13ኛው እስከ 17ኛው ምዕራፍ ያሉት የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፎች ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ያደረጋቸውን የፍቅር ድርጊቶችንና ትምህርቶቹን አጠቃልለው ስለያዙ “የፍቅር ወንጌል” ብለው ይጠሩዋቸዋል፡፡ በእነዚህ ምዕራፎች ብቻ ወንጌላዊው “ፍቅር” እያለ 20 ጊዜ ጽፏል፡፡ የፍቅር ግብር ምሥጢረ ትሕትና የበለጠ የተገለጠው በዚህ ዕለት ነው፡፡ የፍቅር ማዕድ ምሥጢረ ቁርባን የተመሠረተው በዚህ ዕለት ነው፡፡ የምሥጢረ ጸሎት ትምህርትም በስፋት በጌቴ ሴማኒ የአታክልት ስፍራ የተማርነው በዚህ ዕለት ነው፡፡  እኛም ለዛሬ ከወንጌላዊው ጋር በሕፅበተ እግር ስለተገለጠው ስለ ምሥጢረ ትሕትና እንማማራለን፡፡ ምሥጢሩን ይግለጥልን!

FeedBurner FeedCount