በልዑል ገ/እግዚአብሔር
ደመና በወርኃ ጽጌ በበረሃ ሰፈፍ
ከገሊላ ወጥቶ በምስር ላይ ሲከንፍ
ዝናም ጣለለት ለዚያ በረሃ ግለቱ
የሐዲስ ኪዳን ምስራች አማናዊነቱ!
የሄሮድስ ጦር…
ስልምልም ነው ከእሳት አይዋጋም
አዛይቱን
አዛኝቱን እመ መለኮትን አይጠጋም!
ያ ሕጻን ከሰማይ የወረደ ድንቅ ቸር አድራጊ
ባለ እልፍ ሠራዊት ጋሸኛ ከእኩያት ተዋጊ
ብርሃን ያጣ ያ የጨለማ መሬት ብርሃን ወጣለት
በድርሳን ቀለም ተቀልሞለት መዝገብ ተጻፈለት
የስደቱ አንድምታ ውሃ አፍስሷልና ላያደርቀው
ደመና በበጋ በግብጽ ታይቷልና ተአምር ነው!