Wednesday, August 5, 2015
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ
መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ: ገ/እግዚአብሔር ኪደ (መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ውዳሴ፡...
Monday, August 3, 2015
ሆስፒታልና ቤተ ክርስቲያን በንጽጽር ሲታዩ
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ
ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.):- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን!!!
እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን
የምትወዱት ልጆቼ! ተጠራርታችሁ ወደ አባታችሁ ቤት ለመምጣት ያደረጋችሁትን ቅንአት ተመልክቼ ደስ ተሰኝቼባችኋለሁ፡፡ እኔም ይህን
ቅንአታችሁን አይቼ ስለ ነፍሳችሁ ጤና ይበልጥ እንዳስብ አድርጎኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቀዶ ጥገና የሚደረግባት ሐኪም ቤት ናት፡፡
የሥጋ ቀዶ ጥገና ግን አይደለም፤ የነፍስ ቀዶ ጥገና ነው እንጂ፡፡ የምናክመው የሥጋን ቁስል አይደለም፤ መንፈሳዊ ቁስልን እንጂ፡፡
መድኃኒቱም ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ መድኃኒት በምድር ላይ ከሚበቅሉት ዕፅዋት የተቀመመ አይደለም፤ ከሰማያት ከሚመጣው ቃል
እንጂ፡፡ ይህን መድኃኒት በቁስል ላይ ለመጨመር ሐኪሞች አያስፈልጉም፤ የሰባክያነ ወንጌል አንደበት እንጂ፡፡ ቀዶ ጥገናውን ለማከናወን
ብዙ ሰዓታትን አይፈጅም፡፡ ቀዶ ጥገናው ላይሳካ ይችላል ተብሎ የሚጠረጠር አይደለም፡፡ ከጊዜ በኋላ ወይም በሌላ ሕመም ምክንያት
የተደረገው ቀዶ ጥገና ሊከሽፍ ይችላል ተብሎም አይገመትም፡፡ ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒት እንዲህ ዓይነት ችግር ሊያጋጥመው ይችላል፡፡
ሐኪሞች የሚሰጡን መድኃኒተ ሥጋ ለጊዜው ብርቱ ነው፤ ሰውነታችን እያረጀ እንደሚሔደው ኹሉ መድኃኒቱም በጊዜ ሒደት ብርታቱን እያጣ
ይሔዳል፡፡ ሌላ ደዌ ዘሥጋ ሲገጥመንም መቋቋም የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱን የቀመሙት ሰዎች ስለኾኑ፡፡ ከእግዚአብሔር
የሚሰጠን መድኃኒት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ጊዜ ቢቆይም አይበላሽም፤ ጊዜው አያልፍበትም፤ ኃይሉም ብርታቱም ያው
ነው አይቀንስም፡፡
Friday, July 31, 2015
የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ትናንት፣ ዛሬና ነገ
(መቅረዝ
ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 24 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ቀሳውስት ማሠልጠኛ
ተቋም ከተመሠረተ ከ82 ዓመታት በላይ ኾኖታል፡፡ በእነዚህ የአገልግሎት ዘመናቱም በርካታ ታላላቅ
የሃይማኖት አባቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት፣ አባቶች መምህራንና ካህናትን አፍርቷል፡፡ ማሠልጠኛው ጥንታዊው
የሀገራችን ቋንቋና ፊደል ግእዝና ትምህርቱ ተጠብቆ እንዲቆይ ለትውልድም እንዲተላለፍ በማድረግ በኩል ታላቅ ድርሻ አለው፡፡ የቤተክርስቲያን
አባቶችና ምእመናን ኹሉ የቤተ ክርስቲያን አለኝታና ቅርስ መኾኑን በኩራት የሚናገሩለት ተቋም ነው፡፡
ይኼው ማሠልጠኛ በረጅም ጊዜ አገልግሎት ለቤተክርስቲያንም ኾነ ለሀገር ከፍተኛ አገልግሎትና
ጥቅም የሰጠ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዚህን ት/ቤት ትናንት የነበረውን ገጽታ ዛሬ ያለበትንና ወደፊት የሚጠበቅበትን በዚህች አነስተኛ
ጽሑፍ እንዳስሳለን፡፡
Sunday, July 26, 2015
....... ሰላም ገብርኤል.......
በልዑል ገ/እግዚአብሔር
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሰላምታ… የሰላማዊ አካል ስጦታ
................ በጎነት አክብሮት ምሣሌው
የታላቅነት ትርጓሜ የሰሪውን ማንነት
........... አንድ የመሆን ምስጢር ሲለው
ሰላም...!
ያ ነገረ ፈጅ የእስራኤል ባለጠጋ
......... መመረቅ መርገም ቢችልበት
ባላቅ ደስ ሊለው...
የፀጋውን ስጦታ ቅዱሱን ሊረግምበት
.............. አህያውን ይዞ ተጓዘበት
Subscribe to:
Posts (Atom)