(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሰላም...!
ያ ነገረ ፈጅ የእስራኤል ባለጠጋ
......... መመረቅ መርገም ቢችልበት
ባላቅ ደስ ሊለው...
የፀጋውን ስጦታ ቅዱሱን ሊረግምበት
.............. አህያውን ይዞ ተጓዘበት
ያ የሰማይ መልዕክተኛ ...
..... ከነ እሳት ሰይፉ
............ በመንገድ ቢጠብቀው
በምኞት የታወረው በለአም
...............መልአኩን አላየው፡፡
ፍጥረተ ሰብ... ሁለት ጆሮው ቆሞ
.............. አልሰማ ሲል
.............. ጆሮው ላይ ሲተኛ
ፈጣጣ አይን አላይ ሲለው
.............. አልገረዝ ያለው
................ ልቡ ያ ልማደኛ
በእንሰሳ ባለ ደመ ነፍሱ
..........................
በድንጋዩ በበድኑ ቁስ አካል
...................... ያስተምረዋል
ሰሚ ከተገኘ ...
ዲዳዋ አህያ ባትነግረው
................ በቃሏ ባትገስፀው
ሰዉም ሊቀሰፍ
... ጌታም አካሄዱን ሊፀየፈው
ማ በለጠ...?
ሰላማዊ... ያ የሰላም አለቃ
..........................
ሆሣዕና ታጅቦ ሲገባ ሀገረ ሰላም
..........................
በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው
..........................
በእንሰሳ ጀርባ ተቀምጦ ሲታይ
..........................
ሕጻናቱ ..... ቡሩክ አሉ
......... ፈጣሪያቸውን አውቀው አከበሩ
ደቀመዛሙርቱ ..... አጀቧቸው
........... ለዳዊት ልጅ ዝማሬን ዘመሩ
ሕግ አዋቂ ... ተብዮሽ
.................. ማወቅ አለማወቃቸው
የአብርሃም ልጆች እኛ የሚሉ
............... አብርሃም ያልወለዳቸው
ዲቃላዎቹ...!
በጌታ ምስጋና ... አረሩ
አጃቢዎቹን .... አባረሩ
እንግዲህ ልብ በሉ ...
አዋቂ መሣዮች… በትዕቢት ሲጀቦኑ
የቢታኒያ ድንጋዮች ጌታን አመሰገኑ::
ማ በለጠ?
ብርሃን እንጂ እሱ አልባሱ
..........................
እንኳን ሰውን .. ምድርን አበባ ከድኗታል
........... በብጫ በቀይ በነጭ አስጊጧታል
ስድሳ ምዕት ግርፋታቸው
..........................
ሳዶር.. አላዶር.. አምስቱ ቅንዋት
..........................
ይልቅ...
የቅዱሱን ልብሱን በጫጨቁት
..........................
እርቃኑን በእንጨት ሰቀሉት
..........................
ፍጥረተ ሰብ... ሁለት ጆሮው ቆሞ
.............. አልሰማ ሲል
.............. ጆሮው ላይ ሲተኛ
ፈጣጣ አይን አላይ ሲለው
.............. አልገረዝ ያለው
................ ልቡ ያ ልማደኛ
በእንሰሳ ባለ ደመ ነፍሱ
..........................
በድንጋዩ በበድኑ ቁስ አካል
...................... ያስተምረዋል
ሰሚ ከተገኘ ...
የህግ ተቆርቋሪ .. አስመሳዮች
አለ ጨርቅ ባዶውን ቢሰቅሉት ….
…….ግዑዟ ፀሐይ ጨለመችባቸው
የጌታዋን እርቃን አላሳይ ብላቸው
ነፍስ አልባዋ ጨረቃ ደም ለበሰች
............... የአምላኳን ገላ ደበቀች::
ማ በለጠ?
የህያዋን አምላክ ...
በህግ በመጽሐፍ ክታብ
......................በነቢይ
ሰው ...
መጣፉን እንዳያይ ብስራቱን እንዳይሰማ
......................... መስሚያውን ደፍኖታል
ያ የፍቅር አምላክ አሁንም ይናገራል...
ዲዳ እንስሳትን
.............. አፋቸውን ይከፍታል
ግዑዝ ድንጋዮችን
.............. በእልልታ ያዘልላል ::
ማ በለጠ ?
ሰው ..... አሻፈረኝ ቢለው
ነፍስ አልባውን አናገረው
ሰው .......... እንሰሳን መሠለ
እንደውም ….እንስሳው ተሻለ !
'እንካ' .... ያለውን ይቀበላል
'ተሸከም' ያለውን ይሸከማል
ባለ ሁለት ... ባለ አራት እግሩ
... አንገቱን አቀርቅሮ እድሜ ልኩን ይሰግዳል
በቅላፄው .... በድምፀቱ
..........................
ድንጋዩ .... ሕንጻ ማቆሚያ
................ መንገድ ማቅኛ
..........................
በአኮቴቱ በአክብሮቱ በሽብሸባው
..........................
ሰው ግን....!
ወልየ ነዌ... እስራኤል ፀሐይ ያለችው
..........................
ኃይል ፈልጓልና ሊያግዘው
..........................
ክብር ለሚገባው ክብር ሰጥቷልና
..........................
ያ የእግዚአብሔር ሰው በመንፈስ ተቃኝቶ
.................መባነን ባለበት ይባንናልና
ኢያሱ መልአኩን አክብሮ ሰገደ
............... የቅዱሱ ቅዱስ ይከበራልና!
ፍቁረ እግዚእ በፍጥሞ ተመስጦ
... ስለ መጭው ራዕይ ሲመለከት
ያን መልአክ በአይኑ ሲያየው
......... በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለት::
የወዳጁ ልብ በመንፈስ ተቃኝቶ
.... ማድረግ ያለበትን ይመረምራልና
ዮሐንስ መልአኩን አክብሮ ሰገደ
............ የቅዱሱ ቅዱስ ይከበራልና!
የታደለ ትውልድ ...
ለአምላክ ለፈጣሪው …... ለአምላክነቱ
ለቅዱሱ ለመልአኩ ... ለፀጋ ለክብረቱ
ከወገቡ ዝቅ ብሎ
.............. በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ
ጌታው ያከበረውን አክብሮ
.................... የቅዱሱን ዋጋ ወሰደ::
ተመሰጠ...
የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር
የመልአኩን ………... ለመልአኩ
..........................
አስተምህሮውን...
ወንጌል ........... ተናገረ
መምህሩ ... አስተማረ
መጣፉ ........... ተጣፈ
ባንድምታ .......ተደገፈ::
ያልታደለው ግን ...
እንዳይሰግድ ወገቡን አደረቀ
...................... የራሱን ክብር ሽቶ
አንገቱን አደነደነ
................... ወንጌሉን በቅባት ቀብቶ::
ፍጥረተ ሰብ... ሁለት ጆሮው ቆሞ
.............. አልሰማ ሲል
.............. ጆሮው ላይ ሲተኛ
ፈጣጣ አይን አላይ ሲለው
.............. አልገረዝ ያለው
................ ልቡ ያ ልማደኛ
በእንሰሳ ባለ ደመ ነፍሱ
..........................
በድንጋዩ በበድኑ ቁስ አካል
...................... ያስተምረዋል
ሰሚ ከተገኘ ...
ሰላምታ...
ገብርኤል ሆይ ...
ከወገቤ ዝቅ ብዬ
............... በአክብሮት ሰገድኩ
ሳላም ብዬ ... ሰላምታህን
...................... ባንደበቴ ደገምኩ
ሰላም ለከ ገብርኤል...
ሃበ ማርያም ተፈናዊ
ሰናየ ቃል ብሥራታዊ
ሰላም ገብርኤል ...
ለነዳይ ዘትትኤየኖ
ክነፊከ ዘትከድኖ
ሰላም... ሰላም... ገብርኤል!
ስማኝ...!
በአህያ ሰባኪነት ....................... ተሰበክህ
በቢታኒያ ድንጋዮች መምህርነት ...ተነገረህ
በፀሐይ በጨረቃ ጽልመት ….. ተኮረኮምህ
የት አለህ ...?
በእናትህ ንቃ !
ይኸው ከፊትህ ...
ድንጋይ በድንጋይ ላይ… ተነባብሮ
በትልቁ ሕንጻ ስግደት አስተምህሮ::
ከዚህ በላይ
...................... እንዴት ያውራህ?
በአደባባይ ተገርፎ
........... ዳግመኛ ተሰቅሎ ያሳይህ?
....... በእናትህ ንቃ !.......
"አልማር" ያለ ትውልድ...
አልመለስ ላለ ክህደት....
ገብርኤል ከፊት ለፊት ቆሞ…
ሕንጻ ፎቁን ግዑዙን… አቆመላቸው
ወገቡን ሰብሮ ሲሰግድለት አሳያቸው::
ክብር የሚገባውን
......................እንደቃ
እንግዲህ...
በቃሉ አስተምሮሃልና
......................'ስግደ
................ስገድለት::...
© ምንጭ፡- የልዑል ገብረእግዚአብሔር መጽሐፈ ገጽ
No comments:
Post a Comment