Sunday, February 21, 2016

ትንቢተ ዮናስ - ክፍል አንድ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 13 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
መግቢያ፡
ትንቢተ ዮናስ 46 የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ የመጽሐፉ ጸሐፊም ነቢዩ ዮናስ ይባላል፡፡ ዮናስ ማለት ርግብ፣ የዋኅ ማለት ሲኾን የነበረበትም ዘመን በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት /825-784 .../ ነው፡፡ በትውፊት እንደሚነገረው ዮናስ ነቢዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሣው የሠራፕታዋ መበለት ልጅ ነው /1ነገ.1810-24/፡፡ ነቢዩ ዮናስ ምንም እንኳን የእስራኤል ነቢይ ቢኾንም ያስተማረው ከምድረ እስራኤል ውጪ ማለትም በነነዌ ስለኾነ፣ ነቢየ አሕዛብ ይባላል፡፡ ሊቃውንት እንደሚናገሩት ይህቺ ነነዌ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ቆሬ፣ ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 .. ርቀት ላይ ነበረች፡፡ የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ዋና መልእክት እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይሆን የአሕዛብም አምላክ እንደሆነና በንስሐ ወደ እርሱ የተመለሱትን ሁሉ በምሕረት እንደሚጐበኝ ማሳየት ነው፡፡ በመሆኑም በአራት ተከታታይ ክፍል የእያንዳንዱን ምዕራፍ ትርጓሜ በተለይ ደግሞ ከሕይወታችን ጋር እያገናዘብን እንመለከተዋለን፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን ይህን የነነዌን ጾም ከዓቢይ ጾም ኹለት ሳምንት አስቀድመን እንድንጾመው ማድረጋቸው ያለ ምክንያት አይደለምና፡፡ በዚህ መጽሐፍ በሁዳዴ ጾም ልናከናውነውና ሊኖረን የሚገባ የንስሐና የጾም ዓይነት ምን ሊመስል እንደሚባ፣ የእግዚአብሔር ፍቅርና ጥበብ እንደምን የበዛ እንደኾነ፣ ነቢያት እንኳ ድካም እንደነበረባቸውና እንደምን እንደተነሡ እንመለከታለን፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን፡፡

Friday, February 19, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- የመጨረሻው ክፍል (ክፍል አምስት)!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- የመጨረሻው ክፍል (ክፍል አምስት)!:        በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!   ተወዳጆች ሆይ! እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ ለመማማር የጀመርነው ርእስ የሚያልቅ ስላልሆነ እናንተ በይበልጥ ከሊቃውንት ከመጻሕፍት እንድታዳብሩት እ...

Wednesday, February 17, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አራት!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አራት!:        በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ውድ ክርስቲያኖች! የእግዚአብሔር ፍጹም ሰላም ይብዛላችሁ! አሜን! በክፍል ሦስት ትምህርታችን ወደ ስድስት የሚሆኑ ነጥቦችን አይተን ነበር፡፡ ለ...

Monday, February 15, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል ሦስት!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል ሦስት!:       በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!  በክፍል ሁለት ትምህርታችን ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ሥርዓት ከሰዎች ተመርጠው ከሚሾሙት የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ፍጹም ...

Thursday, February 11, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል ሁለት!!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል ሁለት!!: በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!     በክፍል አንድ ትምህርታችን ከሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ሊቀ ካህናት በስፋትና በጥልቀት የጻፈልን የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ እንደሆነ፤ የዚህ ምክንያት...

Tuesday, February 9, 2016

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አንድ!!

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል አንድ!!: በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!        ከ ሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስለ ሊቀ ካህናችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በስፋትና በጥልቀት የምናገኘው በዕብራውያን መልእክት ነው፡፡ ሐዋርያው መልእ...

Friday, February 5, 2016

የክርስቲያን መከራው


በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 27 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ለአንድ ክርስቲያን መከራው ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን  መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልኻለሁ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብርን መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራው ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያገኝ ነውና የክርስቲያን መከራው የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርኻለሁ፡፡

Friday, January 29, 2016

ዕረፍተ ድንግል



በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(ከመጽሐፈ ገጹ የተወሰደ)
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 20 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እመቤታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ የሔደው የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ለማብሠር ነበር፡፡ የድል ምልክት የሆነውን ፍሬው የተንዠረገገ የቴምር ፍሬ የሚያፈራውን ዘንባባ ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ እርሷ ወዳለችበት ይዞ ገብቶ ደስ ይበልሽ ሲላት አሁንም እየሰገዳና እጅ እየነሣ ነበር፡፡ ጌታችን እንዳዘዘውም "ልጅሽና ጌታሽ እናቴ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ጊዜው ደርሷል ብሏል፡፡ ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ቅድስት ሆይ ስለዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ይህን መልካም የምሥራች እነግረሽ ዘንድ ላከኝ፡፡ ብፅዕት ሆይ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ በደስታ እንደሞላሻቸው አሁን ደግሞ በዕረፍትሽና በዕርገትሽ ምክንያት የሰማይ ኃይላት በደስታ ይሞሉ ዘንድ በሰማይ ያሉ ነፍሳትም ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በክብር ያበሩ ዘንድ ምክንያት ትሆኛለሽ፡፡ ደስተኛይቱ ፍስሕት የሚል ማዕረግ ለዘላለም ተስጥቶሻልና ስታዝኝና ስታለቅሽ በኖርሽው መጠን ደስ ይበልሽ፡፡ ጸሎቶችሽና አስተብቁዖቶችሽ በሙሉ በልጅሽ ፊት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፤ ስለዚህም ይህን ዓለም ትተሽው ወደ ሰማይ ትሔጅና ፍጻሜ በሌለው የዘላለም ሕይወት ከልጅሽ ጋር ትኖሪ ዘንድ አዝዟል" ብሎ ዘንባባውንም በእጇ ሰጣት፡፡

Friday, January 22, 2016

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተረጐመው የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ!


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
     በ388 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም መግቢያ ላይ ተጀምሮ፥ በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ የተጠናቀቀው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የኦሪት ዘፍጥረት የትርጓሜ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጹ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ይህ ከሐዋርያት ዘመን አንሥቶ በተመሠረተውና በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እንደ ታነፀ በሚነገረው ፓላዪያ (The Palaia) በተባለ በታላቁ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠው ትምህርት ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን እጅግ የጠለቀ ፍቅርና የሰው ልጅም ምን ያህል ክቡር ፍጥረት እንደ ኾነ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡

Saturday, January 9, 2016

ስግደት (ክፍል 1)


በዲ/ ሕሊና በለጠ ዘኆኅተ ብርሃን


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ 30 ቀን 2008 ..)- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 በፍጹም ልብ በፍጹም ነፍስ በፍጹም ኃይል (ዘዳ.65) የሚወደድ የሆነውን አምላካችን እግዚአብሔርን ስናመልከው ሥጋችንንም፣ ነፍሳችንንም፣ መንፈሳችንንም አስተባብረን መሆን አለበት፡፡ መጻሕፍትን በማንበብ፣ ለብዎትን /ማስተዋልን/ በመጠቀም፣ ዕውቀትን ገንዘብ በማድረግ፣ ነቢብን /ንግግርን/ በማስገዛት፣ ሀልዎትን /መኖርን/ በመሠዋትና በመሳሰሉት እግዚአብሔርን ማምለክ ባሕርያተ ነፍስን ለአምልኮተ እግዚአብሔር ማስገዛት ነው፡፡ ጾም/ከሥጋ ፍላጎት መከልከል/ እና ስግደትን የመሳሰሉት ደግሞ በሥጋ እግዚአብሔርን የምናመልክባቸው፣ ሥጋችንን የምናስገዛባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ (ይህ ማለት ግን ስግደት ለሥጋውያን ብቻ የተገባ ነው ማለት አይደለም፤መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት”/መዝ.977/ እንዳለ መላእክትም የሚሰግዱ ናቸውና፡፡) ፍቅር፣ ቸርነት፣ ምኅረት፣ መመጽወት እና የመሳሰሉት የመንፈስ ሥራዎች ደግሞ ወደ ፍጹምነት የሚወስዱን የሥጋን ድካምና የነፍስን ሐልዮት የምንቀድስባቸው እንዲሁም መንፈሳችንን ለአምልኮተ እግዚአብሔር የምናስገዛባቸው መንገዶች ናቸው፡፡

FeedBurner FeedCount