ገ/እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ኅዳር ፳፬ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- ነቢይ ማለት አፈ እግዚአብሔር፣
መምህር፣ ሰባኪ፣ … ማለት ነው፡፡ ስያሜውም መንፈሰ ትንቢት ላደረባቸው፣ ራዕይን የማየት ጸጋ ለተሰጣቸው እውነተኛ ነቢያት ብቻ
የሚሰጥ ነው፡፡
በብዙዎቻችን
አእምሮ እንደሚታሰበው “ነቢይ ማለት ስለ መፃእያት ብቻ የሚናገር ነው”፡፡ ኾኖም ነቢይ መፃእያትን ከመናገር በተጨማሪ እግዚአብሔር
በየትኛውም ዘመን ለሰው ልጆች ያለውን ሐሳብና ፈቃድ በተለይ ደግሞ ከዘለዓለማዊ ድኅነት ጋር አያይዞ የሚገልጥ ነው፡፡ ለዚኽም ነው
የነቢያትን መጻሕፍት ስንመለከት በውስጡ ብዙ የሕግ፣ የታሪክ፣ የጥበብና የቅኔ ይዘት እንዳለው የምናስተውለው፡፡