በቀሲስ ፋሲል ታደሰ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ጥቅምት 27 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ሥርዓተ አምልኮ ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ ስጦታ ነው፡፡
የሰው ልጅ ከራሱ የኾነ
አንዳች የለውም፤ በጎ የኾነው ኹሉ ከፈጣሬ
ዓለማት ከእግዚአብሔር ያገኘው ነው፡፡ በመኾኑም ፈጣሪያችን መስጠትን እንዳስተማረን ኹሉ እኛም ተገዥነታችንን ከምንገልጥበት አንዱ
ከርሱ የተቀበልነውን በፈቃደኝነት በደስታ በመስጠት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ይኽን
ሲያስረዳ “ኹሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፡
ከእጅህ የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይኽን ያኽል ልናቀርብልህ
የቻልን ማነን? በፈቃዴ ይህን አቅርቤአለሁ”
በማለት ከእግዚአብሔር ያገኘውን ሀብት በደስታ በፈቃዱ ለቤተ መቅደስ
ሥራ እንዲውል መስጠቱን በመግለጽ ስለ ስጦታ ጽፏል
/1ዜና 29÷9-16/፡፡