በቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መስከረም 30 ቀን፣ 2008 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ቃለ እግዚአብሔር
መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡ ይህን መንፈሳዊ መሣሪያ እንዴት እንደምንጠቀምበትና እንደምንታጠቀው ካላወቅንበት ግን በእጃችን ስላለ ብቻ
ምንም ሊጠቅመን አይችልም፡፡ ጠንካራ ጥሩርና ራስ ቍር፣ ጋሻና ሰይፍ አለ እንበል፡፡ አንድ ሰው መጥቶም እነዚህን ታጠቃቸው፡፡ ነገር
ግን ጥሩሩን በእግሩ፣ ራስ ቍሩን በራሱ ላይ ሳይኾን በዓይኑ ላይ፣ ጋሻውን በደረቱ ላይ ሳይኾን በእግሩ ላይ አሰረው እንበል፡፡
እንግዲህ ይህ ሰው እነዚህን መሣሪያዎች ስለ ታጠቀ ብቻ ጥቅም ያገኛልን? ይባስኑ የሚጎዳ አይደለምን? ይህ ለማንም ግልጽ ነው፡፡
ይህ ሰው ተጠቃሚ ያልኾነው ግን ከመሣሪያው ድክመት አይደለም፤ እንዴት መጠቀም እንዳለበት ሰውዬው ስለማያውቅ እንጂ፡፡ በመጽሐፍ
ቅዱስ ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ ትእዛዙን በአግባቡ የማንጠቀምበት ከኾነ የቃሉ ኃይል ምንም ባይቀንስም እኛ ግን ምንም የምንጠቀመው
ነገር አይኖርም፡፡