በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ኅዳር ፳፯ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የምታውቅ ነፍስ ሐሴት ታደርጋለች፡፡ ክርስቶስን፡- “አንተ
መምህረ እስራኤል ነኽ፤ አንተ ንጉሠ ሰማይ ወምድር ነኽ” ትሏለች፡፡ ይኸውም እንደ ፊሊጶስ ማለት ነው /ዮሐ.፩፡፶/፡፡ ይኽቺ ነፍስ
ሐሴትን የምታደርገው ግን በነቢብ ብቻ አይደለም፤ በገቢርም ጭምር እንጂ፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ክርስቶስን ታውቁታላችሁን? እንኪያስ
ትእዛዛቱን ጠብቁ፡፡ ክርስቶስን የሚያሳዝን ገቢር እየፈጸምን እንደምን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ማድረግ ይቻለናል?