(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ማግሰኞ ግንቦት 4 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ውድ መቅረዛውያን እንዴት አላችኁ? ዛሬም ከአንባብያን ከተላኩልኝ ጥያቄዎች
መካከል አንዱን መርጬ በአበው ካህናት የተሰጠውን ምላሽ ይዤላችኁ ቀርቢያለኁ፡፡ ዛሬም መልሱን የሚሰጡን በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኒዓለም
ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል እንዲኹም በታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያም ገዳም የመጻሕፍተ ሐዲሳት የ5ኛ ዓመት ደቀ መዝሙርና የዘንድሮ
ተመራቂ የኾኑት ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ናቸው፡፡ ለአባታችን ተናጋሪ አንደበት ለእኛም ሰሚ እዝነ ልቡና ያድለን፡፡ አሜን!!!
ጥያቄ፡- “ውድ
መቅረዞች! እንዴት አላችኁ? የመቅረዝ አንባቢ ነኝ፡፡ ከምእመናን የምታስተናግዱት ጥያቄ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እኔም ከንስሐ አባት
ጋር የተያያዘ ጥያቄ አለኝ፡፡ እኔ በምኖርበት አከባቢ ከካህናት ጋር አብሮ የመሥራትና የመቀራረብ ነገር አለ፡፡ ይኽም ለእኔ ብቻ
ሳይኾን የሀገሩ ጠባይ የፈጠረው ነው፡፡ እናማ ባለን ቅርርብ በቤተ ክርስቲያን ጕዳይ አለመግባባት ሲፈጠርም ኾነ በሌላ ጕዳይ በአካልም
ኾነ በስልክ እንደ ልብ ስለምናወራ የሰው ስም እያነሣን ስናማ፣ ስናወግዝ አብረን ስለምንውል እንዴት መናዘዝ እችላለኁ?”
አንዳርግ ነኝ ከቺካጎ