Showing posts with label አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ- የዮሐንስ ወንጌል የ39ኛ ሳምንት ጥናት. Show all posts
Showing posts with label አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ- የዮሐንስ ወንጌል የ39ኛ ሳምንት ጥናት. Show all posts

Tuesday, October 16, 2012

አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ- የዮሐንስ ወንጌል የ 39ኛ ሳምንት ጥናት


(ዮሐ.8፡48-59)

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ክፋትን የሚሠራት ሰው በጣም የባሰና አሳፋሪ የሚያደርገው ተሸማቅቆና አፍሮ ራሱን መደበቅ ሲገባው ይባስኑ ለስሕተቱና ለክፋቱ ምክንያትን እየፈለገ ሲቀጥልበት ነው፡፡ አይሁዳውያንም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ የአብርሃም ልጆች አይደላችሁም፡፡ የአብርሃምስ ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤ ከአብ ዘንድ በሕልውና ያየሁትንና የሰማሁትን እውነቱን የምነግራችሁ እኔን ልትገድሉኝ ትሻላችሁና፡፡ አብርሃም እንዲህ አላደረገም፤ ነፍስ አልገደልም፡፡ መግደልስ ይቅርና ልጁን ነበር ለእግዚአብሔር የሠዋው፡፡ ነፍስስ መግደል ይቅርና የወጣው የወረደውን፣ ያለፈው ያገደመውን እንግዳ ነበር ሲቀበል የነበረው፡፡ እንኳንስ እንዲህ ያለ ትምህርት አግኝቶ ነግረውትና አስተምረውት አላምንም ማለት ይቅርና ወጥቶ ወርዶ ነበር ፈጣሪውን ያገኘው፡፡ ስለዚህ እናንተ ልትገድሉኝ እንደምትሹ አባታችን የምትሉት አብርሃም እንዲህ አላደረገም፡፡ በዚያም ላይ ደግሞ ባስተምራችሁ አልተቀበላችሁኝም፡፡ ስለዚህ የአባታችሁኝ የሰይጣን ሥራን ትሠራላችሁና አባታችሁ አብርሃም አይደለም፡፡ እናንተስ ከእግዚአብሔር አይደላችሁም” ብሎ ማየት ያቃታቸውን የመረቀዘ ቁስላቸውን ቢያሳያቸው የባሰ ተናደዱ (ይህን የበለጠ ለማንበብ እዚህይጫኑ)፡፡ በቁስላቸው ላይ ጨው ጨመሩበት፤ “አንተ በእውነት ሳምራዊ ነህ (አይሁዊ አይደለህም) የምንልህ ስለዚሁ አይደለምን? ጋኔን አድሮብሃል፤ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለህም የምንልህስ በዚህ ምክንያት አይደለምን?” ብለው ከወገንነት አውጥተው ከይሁዲነት አግልለው ሰደቡት /ቁ.48/፡፡ እንደ እነርሱ አስተሳሰብ ሳምራዊ ማለት የተናቀ፣ የሚለውን የማያውቅና እንዲሁ የሚዘባርቅ፣ ከአይሁድ ጋር የማይተባበር ይልቁንም የአይሁድን እምነት የሚያናንቅ ነው፡፡ በዚህ አነጋገራቸው ጌታችን ጸረ አይሁድ አቋም እንዳለው አስመስለው ለማቅረብም ሞክረዋል፡፡ አይሁድ ሆይ! ጋኔን ያደረበት ማን ነው? እግዚአብሔርን የሚያከብር ወይስ እግዚአብሔር አብን ያከበረው ወልድን የሚሳደብ? /St. John Chrysostom, Homily 55/፡፡


FeedBurner FeedCount