Thursday, October 4, 2012

ነገረ ማርያም- ክፍል ፩ (መግቢያ)



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ታኅሳስ ፩ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

  
  ይህ የነገረ ማርያም (Mariology) ትምህርት ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰቷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ስላለው የሕይወቷን ዝክረ ታሪክ፣ ስለ እመ አምላክነቷ፣ ስለ ዘላለማዊ ድንግልናዋ፣ በነገረ ሥጋዌ ስላላት ሱታፌ (ድርሻ)፣ ስለ ንጽሕናዋና ስለ ተሰጣት ክብር የምናጠናበት የሃይማኖት ትምህርት ክፍል ነው፡፡

Wednesday, October 3, 2012

በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀመዛሙርቴ ናችሁ


    የዮሐንስ ወንጌል የ38ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.8፡21-47)
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
 (ከቻሉ ጸልየው ይጀምሩ)
  ልበ ስሑታን የሆኑ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ጌታችንን ለመግደል፣ ከሕዝቡ ልብ ለማውጣት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልፈለጉበት ስሕተት የለም፡፡ ሆኖም ንጹሐ ባሕርይ ነውና ይህን ያገኙበት ዘንድ አልተቻላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ነውና በልባቸው የሚያመላልሱትን ስለሚያውቅ ኃጢአታቸውን አውቀው ፍቅሩን እንዲረዱለት፤ የታመሙትን (እነርሱን) ፍለጋ እንደመጣ እንዲያውቁለት በጥበብ፣ በኃይል እንዲሁም በሥልጣን ይነግራቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሚያስፈራሩ ቃላት ሌላ ጊዜም በሚጋብዙ የትሕትና ቃለት ያምኑበት ዘንድ ይጠራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ይህን እንዳያውቁ በምርጫቸው ልባቸውን አደንድነውታልና ይገድሉት ዘንድ ፈለጉ፡፡

Sunday, September 30, 2012

ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት


አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በጊዜው የነበረችው ጨካኝ ንግሥት (ኤውዶክስያ) በክፋት ተነሣስታ በመንፈቀ ሌሊት አስጠርታ በፈረስ በሠረገላ አድርጋ ወደ ደሴተ አጥራክያ ስታግዘው ለራሱ እንዲህ አለ፡- ንግሥቲቱ ከከተማ ስታስወጣኝ ምንም ዓይነት ንዴት አልተሰማኝም፤ ይልቁንም ለራሴ እንዲህ አልኩ እንጂ፡-

Thursday, September 27, 2012

የዕርቅ ቀን


    በእግረ ሕሊናችሁ ከአዲስ አበባ በሰሜን አቅጣጫ 1010 ኪ/ሜ ልውሰዳችሁ፡፡ የጠቀስኩላችሁን ያህል ርቀት ስትጓዙ ዓድዋ ከተማ ትደርሳላችሁ፡፡ ዓድዋ ማለት “ኦድዋ” ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ከበብዋት ማለት ነው፡፡ ከተማዋ ይህን ስም ያገኘችው ዙርያዋ በተስዓቱ ቅዱሳን ገዳማት የተከበበች ስለሆነ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አጠገብዋም ዓዲ አቡን - የአቡን ሀገር የምትባል ሌላ ከተማ አለች፡፡ እዚያ አከባቢ ብቻ የሚበቅል ቲማቲም መሰል አትክልት አለ፡፡ ስሙም “ጸብሒ አቡን” ይባላል፡፡ የአቡን ወጥ እንደማለት ነው፡፡

FeedBurner FeedCount