Monday, June 9, 2014

ጾምን ቀድሱ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ ፪ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡-  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ምእመን ኾኖ ስለ ጾም ምንነትና አስፈላጊነት የማያውቅ አለ ማለት አይቻልም፡፡ ከ፯ ዓመታችን አንሥተን አብዛኞቻችን ከጾም ጋር ተዋውቀናልና፡፡ ጾም የሥጋን ምኞት እንደምታጠፋ፣ የነፍስን ቁስል እንደምትፈውስ፣ ጽሙናንና ርጋታን እንደምታስተምር፣ ከእንስሳዊ ግብር እንደምትጠብቅ፣ ሰውን መልአክ ዘበምድር አድርጋ መንፈሳዊ ኃይልን እንደምታስታጥቅ አብዛኞቻችን ተምረነዋል፤ በቃላችንም እናውቀዋለን፡፡ ነገር ግን በተግባር እግዚአብሔር እንደወደደው የሚጾሙት እጅግ ጥቂቶች መኾናቸው በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የሥጋ ፈቃዳችንን ሳንተው “ስለምንጾም” በሕይወታችን ለውጥ አይታይብንም፡፡

Saturday, June 7, 2014

በዓለ ጰራቅሊጦስ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፥ ግንቦት ፴ ቀን፥ ፳፻፮ ዓ.ም)፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
  “ጰራቅሊጦስ” ማለት በጽርዕ ልሳን “አጽናኝ” ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን በ፩ኛ ዮሐ.፪፡፩ ላይ ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሶ ብናገኘውም፥ አብዛኛውን ጊዜ ግን ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ለሚኾን ለመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ስያሜ ነው /ዮሐ.፲፬፡፲፮/፡፡ ይኸውም የመንፈስ ቅዱስን ግብር የሚገልጥ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ኃምሳ ቤተ ክርስቲያንን በአሚነ ሥላሴ አጽንቶ ዓለምንም ኹሉ ወደ እውነት እንዲመራት መውረዱን የሚያመለክት ነው፡፡

Wednesday, May 28, 2014

ዕርገተ ክርስቶስ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ግንቦት ፳ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ዕለቱን ወደ ሰማይ አላረገም፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ እንደሚነግረን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በ፵ኛው ቀኑ ላይ ነው፡፡ በእነዚኽ ፵ ቀናት ውስጥም ብዙውን ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ እየተገለጠ ብዙ ምሥጢርና ሥርዓተ ሐዲስ አስተምሯቸዋል፡፡ የተማሩትን ኹሉ እንዲጠብቁ፣ ዓለምን ኹሉ በወንጌል መረብ እንዲያጠምዱ ትእዛዝ ሰጥቷቸዋል፡፡

Friday, May 16, 2014

ምክረ አበው ቁጥር 5



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ግንቦት ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
1.  ጥያቄ፡- “ለሰው አፍ ከኮሶና ከነገር ማናቸው ይመራል?"
      ምላሽ፡- "ሲገባ ኮሶ ይመራል፤ ሲወጣ ግን ነገር ይመራል፡፡
2.  ሐሳብህ ብዙ የሚመኝ አንዱን ይዞ የማይሠራ ሲሆንብህ ሰይጣን በጐም ሥራ እንዳትሠራ ባለመሥራትህም እንዳትደነግጥ መልካምን በማሳሰብ እየከለከለ በጥበብ ሰንሰለቱ እንዳሰረህ ዕወቅ፡፡ ስለዚህ አንተ አንድ ሁነህ ሐሳብህን ብዙ አታድርግ፡፡ የምትኖርበትን የማትለቀው አንድ ሥራ ያዝ እንጂ ምኞትህን በየቀኑ አትለዋውጠው፡፡ አንዱን መያዝ አንዱን መልቀቅ የዕብደትና የዝሙት ነውና፡፡

FeedBurner FeedCount