በዲ/ን
ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 21 ቀን
2006 ዓ.ም.)፡- በስመ
አብ
ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
“እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ
በእርሱ እንዲኖር በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላምን
አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና፡፡”
ቆላ 1÷19-20 ይህ የመስቀሉ ደም ለደማውያኑም
ለመንፈሣውያንም ፍጥረት ፍጹምና ዘለዓለማዊ ሰላምን ሰጥቷል፡፡ ታዲያ እኔም በማትከፈል
ሦስትነት በአንድ ሕልውና በምትሆን በእግዚአብሔር ሰላምታ ዘለዓለማዊው ሰላም ይደረግልን ብዬ የአባቴን
የቅዱስ ያሬድን የቀዳሚት ሰንበት ዘወረደ ጾመ ድጓ በጥቂቱ
የተመረጡ ቃላት እነሆ፡፡
ሰላምታዬን በመስቀሉ በተደረገው የሰላም ብስራት የጀመርኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ በዚህ ውሉ
በጠፋበት የሰላም ትርጉም በማይታወቅበት ጊዜያዊ ዓለም ያለውን ሰላም ሳይሆን
ቅዱስ ያሬድ ወደላይ ወደ አርያም
በጾም ከፍ ከፍ ባለው
ሕይወቱ ያንን ዓርብ ዕለት
የተደረገውን የመስቀል የፍቅር አገልግሎት በዛሬው ድርሰቱ ሙሉ ለሙሉ ስለሚያዜም
ነው፡፡ በጾም የተገራች የሰለጠነች ሰውነት ኃጢአት ልጓሟን አይስብም፡፡ ነገር ግን
የመስቀሉ ነገር በዓይኗ ግራ እና
ቀኝ ሆኖ ወደ እውነት
መንገድ ብቻ እንድታይ ያደርጋታል፡፡
እንጀምር ከአባታችን ጋር ጉዞ፡- “ተስፋየ
እምንእስየ ምርጉዝ ለርእሳንየ . . . መስቀል ከልጅነቴ ተስፋ በእርጅናዬ ጊዜ ምርኩዝ
ነው፡፡ ለእውራን መሪያቸው ለአንካሶች ምርኩዛቸው ነው፡፡ እኔ በመስቀልህ እታመነናለሁ እጠጋለሁም፡፡ አቤቱ ለስምህ
አህዛብ ይገዛሉ” 1ቆሮ 1÷18፡፡ ልጅነት እና እርጅና
ኃይል የሌለበት እርዳታ ምርኩዝ ዳዴ የሚያስፈልገው ህይወት ነው፡፡ ወገኖቼ ጾምና ፀሎት
የተለየው ህይወት ታዲያ እንዲሁ ድካም የበዛበት
ነው፡፡ በቃ እርጅና ነው፡፡ በዚህ ጊዜ
ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል የሚሆነን የመስቀሉ ነገር ነው
ከልጅነታችን የምናድግበት ንስሐ የምንገባበት ተስፋ፣ በእርጅናችን የምንደገፍበት በትር ነው፡፡
ስለዚህ አባታችን ከሀዋርያው ጋር የመስቀሉ ቃል ለእኔ
ሞኝነት ሳይሆን ድሕነት ነውና ወደ እርሱ
እጠጋለሁ አለን፡፡ “በኃይለ መስቀሉ ይዕቀበነ. . . በመስቀሉ ኃይል ይጠብቀን የልቦናችንን አይን ያብራልን”
አሜን፡፡
መዝሙረኛው ሊቁ አባት
ከአባቱ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ያዜማል፤ “እመስቀሉ ወሪዶ ውስተ
ሲኦል ሙቁሐነ ፈትሐ . . . ከመስቀሉ ወርዶ የታሠሩትን
ፈታ ነፃነትን ሰበከላቸው” ኤፌ 2÷16 “ጥልን በመስቀሉ
ገድሎ . . .” ማለት ይህ አይደል፡፡
በሚገባን ቋንቋ ልብን በሚመታ
ዜማ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ስለሆንበት
መስቀል ሰበከን፡፡ “መስቀል ሞዐ ሞት ተሞዐ
ኃይለ መስቀሉ አብርሀ - መስቀል አሸነፈ ሞት ተሸነፈ የመስቀሉ ኃይል አበራ፡፡”
ወገኖቼ እንግዲህ ለሁላችን የመስቀል ሞት የመስቀል እንቅፋት በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ተወገደልን፡፡ ዜመኛው
አባት ቅዱሱ የሞትን መሞት የነገረን
በመስቀል የተሰቀለውን ሞታችንን ሞቶ ሞትን ያስወገደልንን ትምክህታችን
እንድናደርግ ነው፡፡ ሐዋርያውም ለዚህ ነው (ገላ
6÷14) “ ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት
ከኔ ይራቅ” ያለን፡፡ ጾም እንደዚህ
ነው ዛሬ 5ተኛ ቀናችን
ነው፡፡ አሁን ልባችንን አርግተን በቃል ጥበብ
ሳይሆን የክርስቶስ መስቀል ነገር ከንቱ እንዳይሆን
(1ቆሮ 1÷17) በመስቀሉ ደም በመሰረታት ቤተክርስቲያን “መስቀል ብርሀን ለኩሉ ዓለም
ዓምዳ ወጽዳ ለቤተክርስቲያን - መስቀል ለዓለም ሁሉ ብርሃን
የቤተክርስቲያን መሠረት” እያልን ፍፁም ሳንለያት ልንተጋ ልንጾም የሚገባን፡፡
በመጨረሻ አባታችን በሰኞ ድርሰቱ
ሲጀምር እንደምናስታውሰው “ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያዕመሩ
እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ በቃሉ -- ከላይ
ከአርያም የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት ወይም ከላይ መውረዱን
አላወቁም ይሆን እርሱስ በቃሉ ሁሉን
የሚያድን ጌታ ነው” እያለ
እንዳዜመልን እናስታውሳለን፡፡ ስለዚህም የዚህን ሳምንት ሲጨርስ “አይሁድሰ ኢያዕመሩ ዘየሐዩ በቃሉ ያበርህ ለኩሉ በዲበ
ዕፀ መስቀሉ - አይሁድስ በቃሉ የሚያድነውን አላወቁም፤ በመስቀሉ ለሁሉ ያበራል”
ብሎን የሳምንቱን ክለሳ የህይወታችንን ዝንጋኤ እንደ ፈሪሳውያን
እንዳይሆን አለማወቃችንን እንዲጦሙ እንዲታዩ እንደተባለላቸው አይሁድ እንዳይሆን የመስቀሉን ድሕነት ነገር እንድናስታውስ በዜማ ገስፆን
በአብ ሰላም በሆነው በመስቀሉ ሰላም ሰላም
ሁኑ ይለናል፡፡
ዘወረደ ተፈጸመ ለእርሱ ልጅነት የማልበቃ ደካማ ስሆን
የማይገባኝን ነገር ስለፃፍኩ ስለእኔ ፀልዩልኝ አሜን በጾሙ
ሰላምን ይስጠን ጾሙን በሰላም ያስፈጽመን አምላከ ቅዱስ ያሬድ
ይጠብቀን፡፡
ይሄን ጉድ ሰምታችሁዋል!!!!!!!!!!
ReplyDeleteአሸናፊ መኮንን ግብረ ሰዶማዊ መሆኑን ታውቃላችሁ?
በርካታ እሱን ሲከተሉ የነበሩ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሁሉ የሚያወሩት ግብረ ሰዶማዊ መሆኑን ነው። በዛ ላይ ውሸታም ሀሰተኛ ነቢይ እና ገንዘብ አፍቃሪ ነው። እድሜውን ሙሉ ሙዳይ ሙጽዋት አቅፎ የሚኖር ሰው ነው። ሰው መስሎን እሱ ጋር ስንመላለስ ሁሌ የሚገርመን ለሙዳይ ሙጽዋት ያለው ፍቅር ነው ከቢሮው ለአፍታም አይለያትም። ከሱ በቀር ማንም አይቆጥራትም። የእግዚአብሔርን ገንዘብ እየበዘበዘ ለግል ጥቅሙ የሚያውል ጀግና ነው። በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ሌላ ምንም ተጨማሪ ገቢ ሳይኖረው ራቫ 4 መኪና ገዝቷል ሱቅ ከፍቷል። ይቅርታ የሚል መጽሀፍ ለስሙ ጽፏል ነገር ግን በምድር ላይ እሱን የሚወዳደር ቂመኛ የለም።
አታግቡ የሁል ጊዜ ምክሩ ነው። ምነው ቢሉ ለሱ እንዲመቸው ነዋ።
በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ የስጋ ጥቅሙን የሚያሳድድ ሸፍጠኛ ግለሰብ አያስፈልግም።
በዛ ላይ ያለበት የእውቀት ችግር በግልጽ የሚታይ ነው። ሊቅ መስሎን ለተጠጋነው የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የህጻን ትምህርት አስተማረን። ከዛ ቢያንስ የሚናገረው ትንሽ እውቀት እንዲኖረው በተለያየ መንገድ ኮሎጅ ገብቶ እንዲማር ለማድረግ ሞከርን መቸ ሰምቶ እራሱን ሊቀ ሊቃውንት አድርጎ ያስቀመጠ ጀግና ነው።
አሁን ደግሞ እንደ ጳጳስ ያደርገዋል አሉ።
በእውነት ብትቀርቡ እና ሕይወቱን ብትመረምሩ እንዲህ ያለ ግለሰብ እንዴት የኛን አገልግሎት ተቀላቀለ? ትላላችሁ። አሳዛኝአሳፋሪ እና አቅሙን የማያውቅ ግለሰብ ነው። እኔ እማዝነው ለበርካታ የዋህና ጨዋ ተከታዮቹ ነው።
የተሃድሶ ነገር ያሳዝናል
እኔ ይህ አሸናፊ መኮንን የሚባል ሰው መኖሩን እራሱ እኔ አላውቅም ግን ፊስቡኩ ሁሉ የዚህ ሰው ግብረሰዶምነት ነው የሚወራው፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን ሰው መከተል አይመቸኝም፡፡ ግን ለምንድን ሰው ክርስቶስን መከተል ትቶ ሰው የሚከተለው? ለዚህ ይመስለኛል ብዙ ክርስቲያን በቀላሉ ለተኩላው የሚበላው፡፡ ይገርማል፡፡ ከዚህ ሰው ትልቅ ትምህርት አግኝተን እራሳችንን መፈተሽ ይገባናል፡፡ የሰውን ኃጢያት ዘርዝሮና ጎልጉሎ ማውጣት የክርስቲያን አስተምሮ አይደለም፡፡ እራሳችንን እንመልከት፡፡ እኛ ማን ነን???????? እኛ በትክክል ክርስትናው ይገልጸናል ወይ???? የሰው እየቃረምን የራሳችንን ሕይወት መፈተሽ ትተናልና፤ እባካችሁ ክርስቲያኖች በዚህ ኃጢያት ተያዙ ብለን የምናወራላቸው ሰዎችን ጸልዩላቸው ነው የተባልነው እንጂ ልክ እኛ እንደማንሰራው አድርገን አደባባይ አውጥተን መሳደቡ መልካም አይደለም፡፡ ክርስትናው ይህንን አይሰብክም፡፡ ፊሪሳውያንን ስራ ተቀብለን ተግባር ላይ ለማዋል የጎበዝነውን ያህል፡፡ ስሙን የተሸከምነው ክርስቶስ እንዲህ ይለናል ‘ማንም ኃጢያት የሌለበት ቢኖር ይህንን ሰው ይፍረድበት’ ብሎ ፍርዱን ለራሳችን ለእያንዳንዳችን ሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ መልእክቱ ስድብን ከሚይዝ ይልቅ እንዲጸለይና እንዲመከር አድርጎ ማስተላለፍ ሲቻል እንደዚህ አድርጎ ማቅረቡ በእውነት ከክርስቲያን አይጠበቅም፡፡ ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን፡፡
ReplyDelete