Wednesday, February 26, 2014

ዘወረደ ዘሠሉስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 17 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
 አባታችን በትናንት ሰኞ ዘወረደ ድርሰቱ አንዳየነው ከላይ በወረደው በጌታ ስም ጀምሮ በዓለም ታንቀንበት የነበረውን ያለፈውን የኃጢአት ገመድ አላቆ የጾምን ክብር በተለይም የዚህን ጾም ክብር ገልጦልናል።በመጨረሻም ተመለሱ ወደ እርሱም ቅረቡ እርሱም አለም ከሚሰጣችሁ ደስታ የተለየ ደስታ ይሰጣችኋል ብሎን ነበረ። ዛሬ ደግሞ በዛው ነፍሳችን በምትሰማው ሠማያዊ ዜማ የሚለን ነገር አለ።


በማክሰኞ ድርሰቱ ብዙውን የሚያዜመው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን ጾምን አልረሳውም። በአጸዱ ብርሃን በሚተከልባት የብርሃን ልጆች በጾም ብርሃንን እንዲያዩ ይለናል። ከአለም ለይቶ በቤቱ የባለቤቱን ጾም እንድናከብር ያዘናል ። እንዲህ እያለእንጹም እንጸልይ በየዋሃትና በፍቅር ለእግዚአብሔር እንሁን፡፡ ቀደምት አባቶች ከኃጢአት እንደዳኑ በአርምሞ ከፈተና እንዳመለጡ (እንደሸሹ)” ጾምን ከጸሎት ጋር አይለያትም፤ ጾም ያለጸሎት ሥጋ ያለነፍስ ብሎ መመሰል እንችላለንና። ጸሎት ደግሞ በልምድ ሳይሆን በተሰበረ ልብ በየውሃት መሆን አለበት ። አሁንም ቢሆን የውሃት ብቻውን አይበቃም። ሁሉን ማሰሪያው ፍቅር ሊታከልበት ይገባል። ለዚህም ነው በዚህ ድርሰቱ ቅዱስ ያሬድ በየገጹ ቢያንስ አንድ ጊዜ ወንድማችሁን ውደዱ የሚል ትእዛዝ ሳይጽፍ ያላለፈው። ፍቅር ያለው ሰው ደግሞ በየትኛውም ጊዜ በምንም ሁኔታ በራሱ ላይ ከአምላኩ ቀጥሎ ስልጣን አለው። አርምሞን ገንዘቡ ያደርጋል። ይህም እርሱን ወደ አላማው ያደርሰዋል ። አላማው የእግዚአብሔር መሆን አይደል? የእርሱ ከሆነ ደግሞ ወጥመድን ፈተናን ሁሉ ያልፋል። አለም የምታዘጋጅለት ሁሉ ከአምላኩ አይለየውም።

 ስለዚህ አባታችን በዚህ ፍቅር ኖሮ ፍቁራንየ እያለ ያዜምልናል፡፡ ድምጹን እንስማየምወዳችሁ ወንድሞቼ የዚህ አለም ንብረት ምን ይጠቅመናል? ምድራዊ መዝገብ እንደሚጠፋ አልሰማችሁምን? ስለዚህ በመንፈሱ በእግዚአብሄር መታመንን ያጸና በሕይወት ይኖራል፡፡ይህን ያለን ደግሞ ንብረት አያስፈልግም ለማለት አይደለም፤ ሁሉ እያለን እንደሌለን እንኑር፡፡ ከአለም ከንቱ መጎምዠት እንጹም እያለን እንጂ። ይህ ይቻላል ? ትሉኝ ይሆናል። እኔ ምን እላችኋለሁ፤ እርሱ ግን መልስ አለው።ዐይን ይጹም፤ ልሳን ይጹም፤ ጆሮም ክፉ ከመስማት ይጹም፤ በፍቅር ይህ ሁሉ ይሁን፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን ደግሞ እኛ በአለም እያለን ከአለም በላይ ከአለም ውጪ እንሆናለን። ያኔ ደግሞ ሰማያዊ ሆንን፣ ጾምን ማለት ነው።
“…በጾም ሙሴ ሕገ እግዚአብሔርን ተሰጠየጾምን ነገር በማክሰኞ ሲፈጽምምእስመ በጾም ወበጸሎት ይሰረይ ኩሉ ኃጢአት በጾም ድኅኑ አበው ቀደምት ኤልያስ ዐርገ ውስተ ሰማያት - በጾምና በጸሎት ኃጢአት ሁሉ ይሰረያልና ፣ የቀደሙ አባቶች በጾም ዳኑ ኤልያስም ወደ ሰማያት አረገባት ። ሙሴን ከሙታን ወስዶ ሕግን በጾም ከእግዚአብሔር ተሰጠ” አለንና ወረድ ብሎ ደግሞ በጾም ሕያዋን ከመሬት ከፍ ብለው በጿሚው ሥጋቸው ሥጋዊውን ምድር አሸነፉ አለን። ስለዚህ ወገኖቼ በጾም ህግን መጠበቅ ብቻ ሣይሆን ከምድራዊ ሕግም በላይ በመሆን ከስጋ ፈቃድ ወጥቶ ወደ ርቱዕ ሕይወት መሸጋገር እንዲቻል ሲያሳውቀን ነው።
 እኔም የማክሰኞ ዜማዬን ከመጨረሴ በፊት አባቴ ዜማውን ሲፈጽም የተናገራቸውን ቃላቶች እነሆየማይጠልቅ ፀሐይ ፣ የማይጠፋ ብርሐን፣ የማያበድሩት ባዕለ ጸጋ ፣ የሐዋርያት ጌጣቸው፣ የችግረኞች ሃብታቸው፣ ለተገፉት መጠጊያቸው ሁልጊዜ እናመሰግንሐለ፡፡ን መሀሪ ንጉሥ በስራው ቸል የማይል።የአብርሀም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ምሕረትሕን አሳየን በአርአያህ የሰራኸውን የፈጠርከውን ሕዝብሕን አታጥፋ አትተው።
በረከቱን ያሳድርብን አምላከ .ያሬድ ይጠብቀን፡፡

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount