Wednesday, February 26, 2014

ዘወረደ ዘሰኑይ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 16 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡-  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

የብሉይ እና የሐዲስ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከጸዋትወ ዜማ መጽሐፍቱ አንዱ በሆነው የድጓ ክፍል ጾመ ድጓ (በጾም ስለሚደረስ ጾመ ድጓ ተብሏል) ስለ ጾም ብዙ ጽፏል። ዛሬ ታዲያ እኔ የምፈቅደው እዚህ ያንን ሰማያዊ ዜማ ስለ ጾም በጾም ለጾመኞች እየተዜመ ብንሰማው ነበረ።ነገር ግን አሁን እሱን ማድረግ አንችልም። ነገር ግን ምንም እንኳን አባታችን በዜማ ያስተላለፈውን መልእክት በጽሁፍ መግለጤ ሰማያዊውን መልእክት ዋጋ እንዳያሳጣው ቢያስፈራኝም በጌታ ባለን ድፍረት እያነበብነው ለፍሳችን በነባቢት ባህሪይዋ ዜማውን እንድትሰማው እርሱ እንዲፈቅድ እየጸለይን ዛሬ ከሰኞ ዘወረደ ድርሰቱ በጥቂቱ የተመረጡ የጾም ቃላትን እያነበብን እንማማራለን። ግእዙን ብጽፈው የሀይለ ቃሉን ኀይል በተረዳነው ነበረ። ነገር ግን ይገባን ዘንድ በአማረኛ እስከገለጠልን ድረስ እናየዋለን


 ቅዱስ ያሬድ የጾሙን ድርሰት ሲጀምርሃሌ ሉያቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ሁሉን የጀመረ ሁሉን የሚስጀምር ሁሉን የፈጸመ ሁሉን የሚያስፈጽም ጾማችንንም እንዲሁ ያድርግልን ሲል ነው።ስለዚህም ቀጠለከላይ ከአርያም የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት ወይም ከላይ መውረዱን አላወቁም ይሆን? እርሱስ በቃሉ ሁሉን የሚያድን ጌታ ነው።ካለ በኋላ መግቢያውን (ድራር) ፈጸመ።

ጾሙን አሁን እንዴት እንየው? አባታችን ቀጠለእንግዲህ ስለ ኀጢአቱ መሰረይ እንደሚጾምና እንደሚጸልይ ጥበበኛ ሰው ሁኑ።መልካም ነገርን ታገኙ ዘንድ በእውነት ሂዱ ሰንበትን አክብሩ መልካም ነገርን ማድረግ ተማሩ… ” ሊቁ እንደሚጾምና እንደሚጸልይ ሰው ሁኑ ብቻ አላለም ። ነገር ግን ጾማችንን በጥበብ ይሁን፤ጥበበኛአለን እንጂ። ዳግመኛም አስተውሉእንግዲህብሎ መጀመሩን፡፡ ከዚህ በፊት ምንም ሁኑ ምንም በቃ ሁሉም ይብቃ፤ ጥበብን ወደ ልባችሁ ጥሯት፤ በጥበብም ጾምን እና ጸሎትን ስለ ኃጣአታችሁ ከዚህ በኋላ ገንዘብ አድርጉ።
አለፍ ብሎእንግዲህያለውን ቃሉን ይገልጠዋልለስጋችሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይብቃችሁ ከእንግዲህስ ወዲህ ጹሙ ጸልዩም ለእግዚአብሔር ተገዙ …” አዎ አሁን ሥጋን ከምኞቱ እና ከመሻቱ ጋር እንሰቅለዋለን። ስለዚህም ከአባቱ ከቅ.ጴጥሮስ የተማረውን መነገር ባለበት ጊዜ ሊቁ ነገረን።የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።”1ጴጥ 43 አሁን ጊዜው የጾም የመገዛት ነው።ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።መዝ 12 ብሎ .ዳዊት የተናገረውን .ያሬድም በፍርሃት እንድንገዛ የአባቱን ቃል ያስተጋባልናል። ያውም በመላእክት ዜማ፡፡ ! ይህን ዜማ አሁን ነፍሴ ሰምታው ደስ ባላት።
 አባታችን ይቀጥላል እኛ ደግሞ እየመረጥን እንናገራለን።ይህች ጾምይህች የተከበረች እና ታላቅ ጾም ለሚያምኑ ሕዝበ ክርስቲያኖች የተሰጠች ናት ለእግዚአብሔር ልጆች መሪ የሆነቻቸው የዚችን ጾም ታላቅነት ተመልከቱ ። በዚህች ጾም እስራኤል ልጆች ባሕርን ተሻገሩባት፡፡ የዚችን ጾም ታላቅነት ተመልከቱ፤ ዳንኤል ከአናብስት አፍ ዳነባት፡፡ የዚችን ጾም ታላቅነት ተመልከቱ፤ ሶስና ከአይሁድ ረበናት ዳነችበት፡፡ የጾምን ክብሯን ታላቅነቷን ተመልከቱ፤ ታላቅነቷን ተመልከቱ ለሰነፎች ሀዘን ለጠቢባን ደስታቸው ናት፡፡ የጾምን ታላቅነት ተመልከቱ፤ የዚችን ጾምእያለ ልንጀምረው የምንደረደርለትን ጾም እያከበረ እያዜመ አስታወቀን።
በጾምስ እንዴት እንሁን እንዳይሉትእርሱ ልብ የሚል የሚያስተውል የሚጾምም ራሱን ዝቅ የሚያደርግም ምስጉን ነው። በሕይወቱ ስለ ሰራው በጎ ስራ ከአምላኩ ክፍያውን ይወስዳል(የሚወስድ ነው)” እያለ እያዜመ ይቀጥላል።
“…እጄ ምድርን መሰረታት ቀኜም ሰማይን አጸና በሕይወት ትኖሩ ዘንድ በጾምና በጸሎት በቀናች ሃማኖት ወደ እኔ ተመለሱ።የሰላም አምላክ በዘመናችሁ ሁሉ ሰላሙን ይስጣችሁ ሕዝ 1830146

ከሰኞ ድርሰቱ ስለ ፆም በመጨረሻ ላይ እንደጅማሬው እንግዲህስ ብሎ ይፈፅማል፡፡እንግዲህስ ይላል እግዚአብሔር በጾምና በጸሎት ወደ እኔ ተመለሱ እኔም በበዛ ምሕረቴ እመለስላችኋለሁ፡፡
ከብዙ ብዙ በጥቂቱ የአባታችንን ቃል ዜማዊ ባልሆነ ኃይል በሌለው ፅሑፍ ልናይ እንደሞከረነው ይህ ፆም የመመለስ የመባረክ የመቅናት ፆም ሊሆን ይገባል፡፡ ሥጋን ከሥጋ ብንለየው ምን ይረባናል? ሰውነታችንን ከመጉዳት በቀር! ከእህል ብቻ ብንከለከል ሰውነታችንን ከመጉዳት በቀር ምን እናገኛለን? ነገር ግን መከልከልስ ከህዋሳት ኃጢአት ነው ። ውሳጣዊ ዐይን ሲሸፈን ውጪያዊ ዐይን ለውስጡ እንደመነጽር ነውና ክፉን አያይም። ውሳጣዊ ጆሮ ሲዘጋ ኃጢአት የማይሰማን እንሆናለን። እጅ ከመስረቅ ያልተገባውን ከመንካት እግር ወዳልተገባው ከመሄድ አንደበትም ምላስም ደግሞ ያልተገባውን ከማውራት ካልቆጠብን የተቀደሰ ጾምን እላችኋለሁ አልጾምንም። እንዲህ ካልጾምን በረከት የለንም። የከበረች ታላቅ ጾምንም አቃለናልና እዳ አለብን ። በበረከቱ ለመጎብኘት ተገቢውን ጾም ለመጾም እናንኳኳ፤ ይከፈትልናል፡፡ በር እንምታ፤ እንገባለን፡፡ እንሞክር፤ ያጸናናል፡፡ እንታገል፤ በእርሱ እናሸንፋለን፡፡ እንነሳ፤ አይጥለንም፡፡
በረከቱን ያሳድርብን
አምላከ .ያሬድ ይጠብቀን፡፡

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount