Saturday, May 2, 2015

ለክርስትና ሃይማኖት ግድ ያለው ሰው ኹሉ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ!



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የተዘጋጀውና “መድሎተ ጽድቅ (የእውነት ሚዛን)” የተሰኘው ድንቅ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ፡፡
ይኽ መጽሐፍ ራሳቸውን “ተሐድሶ” ብለው የሚጠሩት አካላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትምህርትን በተመለከተ በሐሰትና በስሕተት ላሠራጯቸው የስሕተት ትምህርቶች መልስ የሚሰጥ ድንቅ መጽሐፍ ሲኾን በአንጻሩም መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ የኾነው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ትምህርት በጥልቀትና በስፋት የቀረበበት መጽሐፍ ነው፡፡ በውስጡም፡-

  •  የተሐድሶዎች የመዳን ትምህርት እና በመዳን ትምህርት ውስጥ የሚነሡ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተሐድሶዎች ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ እና በቀደምት ሊቃውንት ትምህርት ሲመዘን ምን እንደሚመስል ያገኙታል፡፡ ይኽ ከመጽሐፉ ሰፋ ያለውን ክፍል የሚሸፍን ሲኾን፤
እንደዚኹም፡-
  •  በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መባል ዙሪያ፣
  •  በነገረ ቅዱሳን ዙሪያ፣
  • በገዳማዊ ሕይወትና በምንኵስና ዙሪያ፣
  • በጸሎተ ፍትሐትና በተዝካርና ዝክር ዙሪያ፣
  • ቅዱሳት መካናትን መሳለምን በተመለከተ፣
  • በዓላትን በተመለከተ ሐድሶዎችና መሰሎቻቸው የሚያነሷቸው የስሕተት ትምህርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ እና በአበው ሊቃውንት ትምህርት ተመዝነው ቀርበዋል፡፡


ተሐድሶዎች እነርሱ ነን እንደሚሉት “ኦርቶዶክስ” ናቸውን? ወይስ ፕሮቴስታንት ናቸው? የሚለውን ማንም ሰው እውነቱን ማወቅ በሚያስችለው ኹኔታ በመጽሐፍ ቅዱስና በሊቃውንት ትምህርት ሚዛንነት በጥልቀት ቀርቧል፡፡   
በአጠቃላይ በአንድ በኩል ተሐድሶዎችና መሰሎቻቸው የሚያሰራጯቸውን የፈጠራ ትምህርቶችና ክሶች ከመሠረታቸው ዠምሮ በመመርመር ስሕተታቸውን ከነምንጩና ከነየትመጣው የሚያሳውቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ትምህርት ምንነትም ከመሠረቱ የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ የገጽ ብዛት፡-   524 ገጽ
የመጽሐፉ ዓይነት፡-  B5
ዋጋው፡- 195 ብር
መጽሐፉን በኹሉም መጻሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡ ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከኾነም በእነዚኽ ቁጥሮች መደወል ይችላሉ፡-
  •  0911 47 72 44
  •  0910 07 03 38
  • 0911 48 28 65

1 comment:

  1. የአገልግሎት ዘመንሆን ያርዝምልን ዲያቆን ያረጋል

    ReplyDelete

FeedBurner FeedCount