Tuesday, March 18, 2014

መጻጉዕ ዘረቡዕ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 9 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በአካል ሦስት፣ በሕልውና አንድ በሆነ፣ በመመርመር ገንዘብ በማያደርጉት፣ ምድራዊውን ዓለም ፈጥሮ በሚገዛ፣ ለመንግስቱ ምሥጋና ሰማያዊን ዓለም በፈጠረ በእግዚአብሔር ስም የቤተመቅደስን ምሥጋና የወንጌልንም ቁርባን ለእርሱ እናቀርባለን:: ጉልበት ሁሉ በሚሰግድለት በአምላክ ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን:: (መጽሐፈ ምሥጢር)

Monday, March 17, 2014

መጻጉዕ ዘሠሉስ



በዲ/ንስመኘውጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 8 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱሥ ስም፣ አንድ የናዝራውያን አምላክ፣ የማይለወጥ የሃይማኖት ምሰሶ፣ የማይፍገመገም የመርከባችን አለቃ፣ የማይጨልም የፋናችን ብርሃን፣ ከዘመናት አስቀድሞ በህልውና አንድ የሆነ፣ በስምና በስልጣን የሰለጠነ፣ የመለኮቱ አንድነት በማይለወጥ፣ የመንግስቱ ስፋት በማይወሰን፣ የብልጥግናው ክብደት በማይለካ፣ በአንዱ በእርሱ ስም ሰላም ይደረግልን፡፡

Sunday, March 16, 2014

መጻጉዕ ዘሠኑይ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 7 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 ከባሕሪዩ በማይለወጥ በእግዚአብሔር አብ ስም፣ ከአባቱ በማይለይ በእግዚአብሔር ወልድ ስም፣ በአንደበቱ እስትንፋስ ነቢያትን እፍ ባለባቸው የጸጋውንም ወንጌል ይሰብኩ ዘንድ በተሰጠ ሰረገላዎችም ይሆኑት ዘንድ በእነርሱ ባደረ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ሰላም ለሁላችሁ ይሁን::

መጻጉዕ ዘሰንበተ ክርስቲያን



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 7 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

ሥጋችን በደዌ ተመትቶ መከራ በጸናብን ጊዜ፣ የኢዮብን ሥቃይ ማሰብ አቅቶን በደጅ ተንቀን በወደቅን ጊዜ፣ የምሬታችን ብዛት በአህዛብ ዘንድ ስድብ ሲሆንብን፣ በደጅህ ወድቀን የሚያነሳን ባጣን ጊዜ፣ የወለዱን እንኳን እኛን እስከመጨረሻው መሸከም ከብዷቸው በጣሉን ጊዜ፣ ሊሰሙን ያልወደዱ ነገስታት ሊጎበኙን ያልፈቀዱ ካሕናት በተሠበሰቡ ጊዜ፣ በቁስላችን ላይ ዘይትን በጥዝጣዜያችን ላይ መድኃኒትን የሚያፈሱልንን ባጣናቸው ጊዜ፣ አንተ ሳንጠራህ መጥተህ ሳንጠይቅህ ወደህ ሳንመካብህ መመኪያችን ሆነኸን ከሞት ጥላ በአባታዊ አጠራርህ ልጆቼ ብለህ ጠርተህልጆቼ መዳን ትወዳላችሁን?” ብለህ እንደ ታናሽ አስፈቅደህ መንጻትን በፈቀድን ጊዜ ከደዌያችን ሁሉ ጎንበስ ብለህ አጠብከን፡፡ ስለዚህም ማንም ሊሰጠን ያልፈቀደውን ሰላም ይልቁንም ማንም የሌለውን ሰላም ሰጠኸን:: በዚህ ሰላም ለሁላችሁ ሰላም ይሁንላችሁ!

FeedBurner FeedCount