Thursday, July 9, 2015

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ

መቅረዝ ዘተዋሕዶ : ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ: (መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሐምሌ ፭ ቀን፣ ፳፻፮ ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!   በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል ኹለቱም ታላላቅ ሐዋርያት በሰማዕትነት ያረፉበትን በዓል ...

Sunday, July 5, 2015

ደጃፉንም ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ /ዘፍ.19፡11/


በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
"ወደላይ አቅንተን እንለምን ያን ጊዜ የመለኮትን ነገር ከሚናገሩ መጻሕፍት እውቀት ይገለጽልናል" ይህን ቃል ለቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጅ ለጢሞቴዎስ የላከው በአርዮስፋጎስ (መካነ-ጥበብ) የሚያስተምር የአቴናው ኤጲስ ቆጶስና ለቅዱሳን ሐዋርያት ተከታይ የሆነ ሊቁ ድዮናስዮስ ነው::(ሃይማኖተ አበው ም.10 ቁ.2)
ለዛሬ ያለውን ትምህርታችንን ከላይ ያነሣነውን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የምናይ ሲሆን ለዚሁም በቸርነቱ ብዛት እውቀትን ጥበብን ምስጢርንና ማስተዋልን ለሰው ልጆች ሁሉ የሚገልጥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የተሰወረውን ገልጦና የተከደነውን ከፍቶ የቅዱሳት መጻሕፍትን ጥልቅ ሃሳብ እንድንረዳ ይርዳን!

Thursday, July 2, 2015

የንስሐ አባቴ ኃጢአቴን ቀለል አድርገው ስለሚነግሩኝ ንስሐ ለመግባት እቸገራለሁ፡፡ ምን ላድርግ?



(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 25 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ውድ መቅረዛውያን እንዴት አላችሁ? ዛሬም ከአንባብያን ከተላኩልኝ ጥያቄዎች መካከል አንዱን መርጬ በአበው ካህናት የተሰጠውን ምላሽ ይዤላችሁ ቀርቢያለሁ፡፡ ዛሬም መልሱን የሚሰጡን በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል እንዲሁም መጋቤ አእላፍ ቀሲስ ፋሲል ታደሰ ናቸው፡፡ ለአባታችን ተናጋሪ አንደበት ለእኛም ሰሚ እዝነ ልቡና ያድለን፡፡ አሜን!!!
ጥያቄ፡-  “ውድ የመቅረዞች አዘጋጆች! እንዴት አላችሁ? የመቅረዝ ዘተዋሕዶ አንባቢ ነኝ፡፡ ከምእመናን የምታስተናግዱት ጥያቄ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እኔም ከንስሐ አባት ጋር የተያያዘ ጥያቄ አለኝ፡፡ ለካህናት እንዲህ አደረግኩ ብዬ ስናገር፡- ‘ምንም ችግር የለውም፡፡ ይህቺ’ማ ምን አላት?’ እያሉ በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ሌላውን ለመናገር ቸገረኝ፡፡ ምን ላድርግ?”
አንዳርግ ነኝ ከቺካጎ

Monday, June 22, 2015

ሒዱ እንጂ ተቀመጡ አልተባልንም (ክፍል ኹለት)



በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
(መዝረቅ ዘተዋሕዶ፣ ሰኔ 16 ቀን፣ 2007 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
ኹለተኛው በይሁዳ ነው!
ይሁዳ የኢየሩሳሌም አውራጃው ነው፡፡ የይሁዳ አውራጃ ዋና ከተማም ኢየሩሳሌም ነች፡፡ ከኢየሩሳሌም ይሁዳ ይከፋል፤ ከሰማርያ ግን ይሻላል፡፡ ምክንያቱም ኢየሩሳሌም ዋና ከተማዋ ነች፣ ጌታም የተወለደው በይሁዳ አውራጃ በቤተ ልሔም ነው፡፡ የተሰቀለው፣ የሞተው፣ የተቀበረው፣ ያረገው፣ መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከው በኢየሩሳሌም ከተማ ነው፡፡ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ነገር በይሁዳ አውራጃ የተሻለ ይወራል፤ ይነገራል፡፡ የሚያውቁት ዘመድ ይኖራል፡፡ የሐዋርያትና የይሁዳ ቋንቋ ተመሳሳይ ነው፡፡ የይሁዳ ባሕልና የኢየሩሳሌም ባሕል ተመሳሳይ ነው፡፡ ከሰማርያ ቢሻልም ከኢየሩሳሌም ግን ይከፋል፡፡

FeedBurner FeedCount